ሳምሰንግ ውሃ የማያስገቡ ስማርት ስልኮችን አስተዋወቀ

0
1024
ሳምሰንግ በኖት 7 ስማርት ስልኩ ከገጠመው ኪሳራ በኋላ ትናንት አነስተኛ ዋጋ ያላቸውና ውሃ የማያስገቡ ስማርት ስልኮችን አስተዋወቀ።

ስማርት ስልኮቹ በዚህ ወር መጨረሻ ወደ ገበያ ይገባሉ ተብሏል።

ኩባንያው ያስተዋወቃቸው ሶስት የጋላክሲ ኤ ስማርት ስልኮች በመጀመሪያ በሩስያ ለገበያ ቀርበው ወደ ሌላው የአለማችን ክፍል እንደሚሰራጩ ተገልጿል።

ጋላክሲ ኤ3፣ ኤ5 እና ኤ7 የሚል ስያሜ የሚኖራቸው ስማርት ስልኮቹ በስክሪን ስፋታቸው መጠን ይለያያሉ።

ኤ3 ስማርት ስልኩ 4 ነጥብ 7 ኢንች የስክሪን ስፋት ያለው ሲሆን ኤ5 5 ነጥብ 2 እንዲሁም ኤ7 5 ነጥብ 7 ኢንች ስክሪን አላቸው።

አዳዲሶቹ ስማርት ስልኮች ውሃ እና አቧራ የማያስገቡ መሆናቸውም ነው የተነገረው።

16 ሜጋ ፒክስል ካሜራ እና በየትኛውም አቅጣጫ ፎቶ ግራፍ ማንሳት የሚያስችል የፊት ካሜራም ይኖራቸዋል።ሳምሰንግ ትናንት ያስተዋወቃቸው “ኤ” ሲሪየስ ስማርት ስልኮች 32 ጊጋ ባይት ውስጣዊ የመያዝ አቅም (ኢንተርናል ስቶሬጅ) ቢኖራቸውም ሚሞሪ ካርዶችን አይቀበሉም ተብሏል።

የስልኮቹ ዋጋ እስካሁን ይፋ አልተደረገም። ይሁን እንጂ ከ400 የአሜሪካ ዶላር በታች እንደሚሆን ይገመታል።

ይህም ከጋላክሲ ኤስ ስልኮች በ50 በመቶ ያነሰ መሆኑ ነው የተገለፀው።

ሳምሰንግ በጋላክሲ ኖት 7 ስማርት ስልኩ መፈንዳት ችግር በቢሊየን ዶላሮች ኪሳራ አጋጥሞታል።

እሳት የሚፈጥረውን የዚህን ስማርት ስልክ ችግር ለማወቅ ያደረገው ምርመራ መጠናቀቁ ቢነገርም ኩባንያው እስካሁን ለህዝብ ይፋ አላደረገውም።

 

READ  የእጅ ሙቀትን የሚጠቀም የሞባይል ቻርጀር በቅርቡ ወደ ኢትዮጵያ ገበያ ይገባል ተባለ

NO COMMENTS