አፍጋናዊቷ ለብቻዋ ገበያ በመሄዷ በሰይፍ መገደሏ ተዘገበ

0
1794
አፍጋናዊቷ ለብቻዋ ገበያ በመሄዷ
ቡድኑ ሴቶችን በአጠቃላይ ከባለቤታቸው ወይም ቅርብ የወንድ ቤተሰባቸው ጋር ካልሆነ ወደውጪ እንዳይወጡ የሚል ጥብቅ ህግ በሚቆጣጠራቸው አካባቢዎች ማስፈኑ ይነገራል፡፡

አሁንም ድረስ ጽንፈኛ ነው የሚባለው ቡድን ታሊባል በሚቆጣጠራቸው የአፍጋኒስታን አካባቢዎች እጅግ አሰቃቂ ፍርዶች በሰዎች ላይ ይፈጸማሉ ይባላል፡፡ ቡድኑ ሴቶችን በአጠቃላይ ከባለቤታቸው ወይም ቅርብ የወንድ ቤተሰባቸው ጋር ካልሆነ ወደውጪ እንዳይወጡ የሚል ጥብቅ ህግ በሚቆጣጠራቸው አካባቢዎች ማስፈኑ ይነገራል፡፡

ሰንደይ ኤንድ ዴይሊ ኤክስፕረስ በሰሞነኛ ዜናው ይህን ህግ የተላለፈች አንዲት አፍጋናዊት በሰይፍ መገደሏ ተናግሯል፡፡ የ 30 አመቷ ሴት ለብቻዋ ባሏን ሳታስከትል ገበያ በመሄዷ ይህ አሰቃቂ ሞት እንደገጠማት ዘገባው ገልጿል፡፡ ከትዳሯ ልጆች ያላፈራችው ግለሰቧ ባለቤቷ ወደ ጎረቤት ሀገር ኢራን ማምራቱ ብቻዋን ገበያ ለመውጣት ምክንያት እንደነበር የተናገረው ዘገባው ነገር ግን መንገዷ ላይ ጥቃት እንደደረሰባትና በሰይፍ መገደሏን ነው የተናገረው፡፡

ግለሰቧ የተገደለችበት ሳርኤ ፑል የተባለው ይህ የአፍጋን አካባቢ አሁንም ድረስ በታሊባኖች እጅ እንደሚገኝ የተናገረው ዘገባው ከባላቸው ውጪ ወይም ወንድ ሳያስከትሉ በሚንቀሳቀሱ ሴቶች ላይ ይህን መሰሉ ዘግናኝ ግድያ ሲያጋጥም የመጀመሪያ እንዳልሆነ ያስረዳል፡፡ ይሁን እንጂ የአካባቢው የታሊባን ሀይሎች ይህን የግለሰቧን ግድያ እኛ አልፈጸምንም ማለታቸው ነው የተነገረው፡፡

በካንዳሀር በቅርቡ ለአንድ የግል ድርጅት በጥበቃ ባልደረባነት የሚሰሩና ሴቶችን በር ላይ የሚፈትሹ 5 ሴቶች ወደስራ ሲሄዱ የተሳፈሩበት መኪና ላይ ያልታወቁ ሰዎች ተኩስ ከፍተው ገደሏቸው፡፡ የአፍጋን እንስቶች ይህን መሰሉ ዘግናኝ ሞት እጣቸው የሆነ ይመስላል የሚለው ዘገባው አምና 5 ሺህ የነበረው ይህን መሰሉ በሴቶች ላይ የሚፈጸም ጥቃት ዘንድሮ በስምንት ወራት ብቻ 3,700 ጥቃት መፈጸሙን በመጥቀስ የዛች ሀገር ሴቶች ሰቆቃ መጨመሩን ለማስረዳት ይሞክራል፡፡express

READ  Ethiopia, Zimbabwe, Rwanda Tops in Ibrahim index of African governance

NO COMMENTS