በውፍረት ችግር የተነሳ ባሏንና የቀደመ ህይወቷን ያጣችው በጠንካራ ስራዋ ሁሉንም አሸንፋለች

0
2800
በውፍረት ችግር የተነሳ ባሏንና
በውፍረት ችግር የተነሳ ባሏንና የቀደመ ህይወቷን ያጣችው በጠንካራ ስራዋ ሁሉንም አሸንፋለች

ገና የ 34 አመት እድሜ ያላት በአሜሪካ ቴክሳስ ምትኖረው ቤትሲ አያላ በወሊድ የተነሳ ለውፍረት ችግር ትዳረጋለች፡፡ በልጅ የተባረከ የሞቀ ትዳር የነበራት ይህች ሴት ከወሊድ ጋር በተያያዘ አለቅጥ መወፈር ትጀምራለች፡፡ ይህን ጊዜ ሁሉም ነገር መለወጥ እንደጀመረ የሚናገረው ዴይሊ ሜል ባል በላይዋ ላይ ሴት እንደደረበባት ይናገራል፡፡

ይህ ሳያንሳት አሁን ላይ እንደ እድል በምትቆጥረው በአንድ መጥፎ አጋጣሚ ባለቤቷ ከውሽማው ጋር በስልክ የተለዋወጣቸውንና በውፍረቷ የተነሳ እጅግ የሚያዋርድ ማንጓጠጥና ዘለፋን የያዙ መልእክቶችን ቤትሲ ተመለከተች ይላል ዘገባው፡፡ ይህን ተከትሎ መፈጠሯን እስክትጠላ ራሷን እንደጠላችና እንዳለቀሰች የተናገረችው ቤትሲ የኋላ ኋላ ግን ከማልቀስና ከመጸለይ የዘለለ እርምጃ መውሰድ እንዳለባት ተገንዝባ ህይወቷን ለመለወጥ መብቃቷን መስክራለች፡፡

በእህቷ እርዳታ በእልህ ተነሳሳት ስፖርት መስራት የጀመረችው ቤትሲ በሳምንት ስድስት ቀናት ጂምናዚየም አዘውታሪ ሆነች፡፡ ከዚህ በተጨማሪ የአካል ብቃት እንቅስቃሴን የሚጠይቁ ውዝዋዜዎችን ታዘወትር እንደነበር የተናገረችው ቤትሲ ዛሬ ላይ ክብደት ቀንሳ ማንንም ወንድ የሚያስጎመጅ ሸንቃጣ ተክለ ቁመናን መያዟ ተዘግቧል፡፡

አሁን ላይ ባሌ ያን ሁሉ ውርደት ያከናነበኝን ቀን አመሰግናለሁ ስትል በእልህ ህይወቷን እንድትለውጥ የረዳትን ያን የተረገመ የስልክ ቴክስት ያየችበትን አጋጣሚ ታስታውሳለች፡፡ በፈትነት ቢሆንም በደስታ ልጇን እያሳደገች ምትገኘው ቤትሲ ከ 17 አመት እድሜዬ ጀምሮ 14 አመታት የከፈልኩለት ፍቅርና ትዳር በገጠመኝ ከልክ በላይ በሆነ ውፍረት አጥቻቸዋለሁ በማለት ከራሷ ክፉ ገጠመኝ ተነስታ ሰዎች ሁሌም ህይወታቸውን ለማሻሻል መታገል እንደሚኖርባቸው ትመክራለች፡፡ dailymail

READ  ጀግናው አትሌት ቀነኒሳ በዱባይ ማራቶን ይካፈላል ተባለ

NO COMMENTS