‹‹እንደ እናት›› ፊልም ለአራት ቀን ብቻ ታይቶ ምን ሆኖ ታገደ ?

0
2418
‹‹እንደ እናት ፊልም››
‹‹እንደ እናት›› ፊልም ምን ሆኖ ታገደ ?

‹‹እንደ እናት›› ፊልም ለአራት ቀን ብቻ ታይቶ ምን ሆኖ ታገደ ?  – መታየት በመጀመረ በአራተኛው ቀን የታገደው ‹‹እንደ እናት ፊልም›› የተሰኘው እና ዓለም ሰገድ ተስፋዬን ጨምሮ ታዋቂ ተዋናይን  የሚተውኑበት ፊልም የታገደበት ምክንያት ምንድነው ? የሚለውን ለማጣራት የታዲያስ አዲስ የሬድዮ ፕሮግራም ከፊልሙ ፕሮዲውሰር አቶ ኤልያስ ፋንታሁን እና ፊልሙና ካሳገደው አቶ ቴዎድሮስ ሃይሉ ጋር ቆይታ አድርጎ ነበር፡፡

የፊልሙ ፕሮዲውሰር ኤልያስ ፋንታሁን ፊልሙን ያሳገደ ግለሰብ ከፊልሙ ጋር ምንም አይነት ግንኙነት የሌለው ሰው መሆኑን እና ፈልሙ በፍርድ ቤት የታገደበትን ምክንያም በውል አላውቀውም ማለታቸው ተሰምቷል፡፡

‹‹ፍቅር ተራ›› እና ‹‹ግዜ ቤት››  የተሰኙ ፊልሞችን ፕሮዲውስ እንዳደረገ የተናገረው ኤልያስ ፋንታሁን ከዚህ ቀደም መሰል ችግር አጋጥሞት እንደማያውቅ ተናግሯ፡፡

ፊልሙን ካሳገደው ግለሰብ ጋር ጉዳዩን በሽማግሌ ለመፍታት ያደረገው ጥረት አለመሳካቱን እና ፊልሙ በቅርቡ እገዳው ተነስቶለት ለተመልካች ይቀርባል የሚል ተስፋ እንዳለውም ተናግሯል፡፡

በፊልሙ በርካታ ታዋቂ የፊልም ባለሞያዎች የተሳተፉበት ሲሆን ከእነዚህ ውስጥም ተዋናይ አለምሰገድ ተስፋዬ ፤ እድለወርቅ ጣሰው ፤ ሃና ተረፈ እና ሌሎችንም መጥቀስ ይቻላል፡፡

በሌላ በኩል ፊልሙን ያሳገዱት አቶ ቴዎድሮስ ሃይሉ ለሬድዮ ፕሮግራሙ በስልክ በሰጡት አስተያየት የፊልሙ ፕሮዲውሰር አቶ ኤልያስ ተስፋዬ ከዚህ በፊት ፕሮዲውስ ባደረጉት ‹‹ግዜ ቤት›› በተሰኘው ፊልማቸው ከከሳሽ ድርጅት ‹‹አቢሶ ሲኒማ ኢንተርቴይመንት›› ጋር የተለየ ውል እንደነበራቸው አስታውሰው በውሉ ላይ የነበረውን ክፍያ እንዳልፈጸሙ ተናግረዋል፡፡

የከሳሽ ድርጅት የፊልም ስራዎች ዲጂታል በሆነ ሲስተም ወደ ሲኒማ ቤት እንዲገቡ እና የፊልም ስርቆትን ለመከላከል የሚያስችል ስራ እንደሚሰራም አቶ ቴዎድሮስ ሃይሉ ጠቁመዋል፡፡

READ  ኮሜዲያን ፍልፍሉ እና ደምስ በገና የበዓል የመዝናኛ ፕሮግራም

ጉዳዩን በሽምግልና ለመያዝ ያደረጉት ጥረትም በፊልሙ ፕሮዲውሰር መሰናከሉን አቶ ቴዎድሮስ ተናግረዋል፡፡

 

NO COMMENTS