የፕላስቲክ ኮዳዎች በደቡብ አፍሪካ ለተማሪ ቤት መገንቢያነት ዋሉ ተባለ

0
808
የፕላስቲክ ኮዳዎች በደቡብ አፍሪካ

ጥቅም ላይ የዋሉ የፕላስቲክ ኮዳዎችና ማሸጊያዎች አካባቢን በመበከል ትልቅ ጉዳት ያስከትላሉ፡፡ በተለይ እንደ አፍሪካ ባሉ ታዳጊ አህጉራት ይህን መሰሉን ጎጂ የአካባቢ በካይ ቁስ ለማስወገድ ከፍተኛ ወጪንና ልፋትን መጠየቁ አይቀሬ ነው፡፡

ከወደ ደቡብ አፍሪካ የተሰማው ዜና ግን ለዚህ ችግር አዲስ መፍትሄን ይዞ ብቅ ያለ ይመስላል፡፡ በዛች ሀገር ከወዳደቁ የፕላስቲክ ኮዳዎች ትምህርት ቤት ተገንብቷል መባሉ በእጅጉ እያነጋገረ ይገኛል፡፡

የወዳደቁት የፕላስቲክ ኮዳዎች አሁን ላይ ተገጣጥመውና ግድግዳና ማገር ሆነው 45 ክፍሎች ያሉት ተማሪ ቤትን ለመስራት አስችለዋል ሲል ሲሲቲቪ የዜና ወኪል ኒውስ 24ን ጠቅሶ ዘግቧል፡፡

አንድ ክፍል ለመስራት 90 ሺህ የፕላስቲክ ኮዳዎችን መጠቀም ያስፈልጋል ዘገባው ይላል፡፡ ይህ ፕሮጀክት ከዛሬ 5 አመት በፊት በስራ ላይ የዋለው የቦትል ቱ ቢውልድ ፕሮጀክት አካል መሆኑን የተናገረ ሲሆን በካይ ስለሆኑ የፕላስቲክ ቁሶች ጠንቅነት የማስተማር አላማ ያለውና ዳግም ወደጥቅም እንዲገቡ የማበረታታት እቅድ አንግቦ እንደሚንቀሳቀስ ተነግሯል፡፡

ከዚህ ቀደም በናይጄሪያ በግለሰቦች ተነሳሽነት ከፕላስቲክ ኮዳዎች የተሰሩ ተመሳሳይ የቤት ግንባታዎች መታየታቸው አይዘነጋም፡፡ የፕላስቲክ ማሸጊያዎችና ኮዳዎች ገአወጋገድ ጉዳይ ትልቅ ራስ ምታት በሀጆነበት በዚህ ወቅት ይህን አይነት የፈጠራ ስራዎች መታየታቸው በጎ መሆኑን ሲሲቲቪ ተናግሯል፡፡ cctv

Read More:

Turning plastic bottles Into the building blocks of education
A small company in the east of Gauteng has figured out a way to turn recycled plastic into functional building material that can be used to build classrooms countrywide.

Bottles2Build turns plastic waste into square-shaped bottles which interconnect, helping to create structures.

READ  ዩጋንዳ የ 1.28 ቢሊዮን ዶላር የእርሻ ፕሮጀክት ልትሰራ ነው

“What is really nice about the initiative is that, not only is it about keeping plastic out of our landfills, because plastic is very harmful for the environment, but also uplifting local disadvantaged communities,” said Bottles2Build’s brand development manager Kevin Petitt.

Bottles2Build was launched about five years ago with the aim of finding a way to use the millions of plastic bottles which would otherwise end up piling up in landfills across Gauteng.

NO COMMENTS