የመንግስት አመራሮችን ጨምሮ በሙስና ወንጀል የተጠረጠሩ 130 ግለሰቦች በቁጥጥር ስር ዋሉ

0
8912
በሙስና

በሙስና ወንጀል የተጠረጠሩ 130 ግለሰቦች በቁጥጥር ስር መዋላቸውን የፌደራል ፖሊስ ኮሚሽን አስታወቀ።

ኮሚሽኑ የሙስና ወንጀሎችን መመርመር ከጀመረ በኋላ ከህዝብ፣ ከመንግስትና መንግስታዊ ካልሆኑ ተቋማት 260 የሚሆኑ የሙስና ወንጀል ጥቆማዎች ደርሰውታል።

ኮሚሽነር ጀኔራል ልዩ አማካሪ ኮማንደር ደስታ አስመላሽ በሰጡት መግለጫ እንዳስታወቁት፤ በሙስና ወንጀል ከተጠረጠሩ 260 ግለሰቦች መካከል 130ዎቹ በቁጥጥር ስር ውለዋል።

ከእነዚህም ውስጥ 13 ተጠርጣሪዎች ላይ የሃብት ንብረት እገዳ መጣሉን ተናግረዋል።

በስምንት ትላልቅ አክሲዮኖች፣ በአራት ህንጻዎች፣ በ49 ተሽከርካሪዎች፣ በ22 መኖሪያ ቤቶችና በሁለት ፋብሪካዎች ላይ እገዳ መደረጉንም ኮማንደር ደስታ ገልጸዋል።

የተቀሩት የሙስና ወንጀል ተጠርጣሪዎች ደግሞ በቁጥጥር ስር ውለው ምርመራ እየተደረገባቸው ሲሆን፥ ከተጠርጣሪዎቹ መካከል የመንግስት አመራር አካላትና ባለሙያዎች እንደሚገኙበትም ነው የገለጹት።

በዚህ ሳምንት መጀመሪያ ላይ የአዲስ አበባ ፖሊስ ኮሚሽን በሙስና ወንጀል የተጠረጠሩ 125 ግለሰቦችን ከትናንት በስቲያ በቁጥጥር ስር አውሏል። (ኤፍ ቢ ሲ)

READ  የትግራይ ክልል የዓረና የስብሰባ ፈቃድ ጥያቄ አልደረሰኝም አለ

NO COMMENTS