በሰመራ ዩኒቨርሲቲ በደረሰ የእሳት አደጋ ግምቱ ያልታወቀ ንብረት ተቃጠለ

0
906
በሰመራ ዩኒቨርሲቲ

በሰመራ የኒቨርሲቲ ትናንት ማታ በደረሰ ድንገተኛ የእሳት ቃጠሎ ለጊዜው ግምቱ ያልታወቀ ንብረት መውደሙን የአፋር ክልል ፖሊስ ኮሚሽን አስታወቀ።

የክልሉ ፖሊስ ኮሚሽን ምክትል ኮሚሽነር አሊዲኒ አለሳ ለኢዜአ እንደገለጹት፣ ትናንት ማታ ከምሽቱ 1፡30 አካባቢ የዩኒቨርሲቲው የዕቃ ግምጃ በእሳት ተቃጥሏል።

በእዚህም በግምጃ ቤቱ የነበሩ ለጊዜው ግምታቸው ያልታወቀ ንብረቶች መውደማቸውን ተናግረዋል።

የእሳት አደጋው በሰው ላይ ምንም አይነት ጉዳት ያላደረሰ ሲሆን፥ የአደጋውን ትክክለኛ መንስኤ የሚያጣራ የፌደራል የእሳት አደጋ ምርመራ ቡድን ነገ ወደስፍራው ያመራል ተብሏል።

እንደ ኮሚሽነሩ ገለጻ እሳቱ ወደሌላ ሕንጻ ሳይዛመት ከምሽቱ 5፡30 ላይ መቆጣጠር ተችሏል።

የሰመራ ዩኒቨርሲቲ ፕሬዚዳንት አቶ አደም ቦሪ በበኩላቸው፣ በቃጠሎው በዕቃ ግምጃ ቤት ውስጥ የነበሩ የተሽከርካሪ ጎማዎች፣ የስፖንጅ ፍራሾች፣ የውሃ መሳቢያ ሞተሮች፣ ላፕቶፖችና ሌሎች ዕቃዎች ሙሉ ለሙሉ መውደማቸውን ገልጸዋል።

ከንብረቶቹ በተጨማሪ መጋዘኑ ሙሉ ለሙሉ ከጥቅም ውጭ መሆኑን የገለጹት ፕሬዚዳንቱ፣ በእሳት አደጋው ምክንያት የመማር ማስተማር ስራው አለመስተጓጎሉን አስረድተዋል። (ኤፍ ቢ ሲ)

READ  ወደግል ከተዛወሩ የልማት ድርጅቶች 2.2 ቢሊዮን ብር ዕዳ መሰብሰብ አልተቻለም

NO COMMENTS