“ተመስገን ሕመሙ ፀንቶበታል” የጋዜጠኛ ተመስገን ደሳለኝ ቤተሰቦች

0
1153
“ተመስገን ሕመሙ ፀንቶበታል
“ተመስገን ሕመሙ ፀንቶበታል” የጋዜጠኛ ተመስገን ደሳለኝ ቤተሰቦች

በዝዋይ ማረሚያ ቤት የሦስት ዓመት እስራት ተፈርዶበት የሚገኘው ጋዜጠኛ ተመስገን ደሳለኝ ሕመሙ ፀንቶበት ወደ ሆስፒታል ተወስዶ እንደነበር የገለፁት ቤተሰቦቹ፤ የማረሚያ ቤት ባለሥልጣናት የጤንነት ሁኔታውን አስመልክቶ መረጃ እንደከለከሏቸው ቤተሰቦቹ አስታወቁ።በእስር ላይ የሚገኘው ጋዜጠኛ ተመስገን ደሳለኝ ጤንነትን እንዳንከታተል ተከለከልን ሲሉ ቤተሰቦቹ ተናገሩ
ማረሚያ ቤት ለጥየቃ እንደከለከላቸው ገልጸዋል፡፡ ጋዜጠኛውን ሰሞኑን ለመጠየቅ በሞከርንበት ወቅት በማረሚያ ቤቱ ተከልክለናል ሲሉም ተናግረዋል፡፡ ከ 11 ቀናት በፊት አግኝተነው ነበር ሲሉ ለቪኦኤ የአማርኛ ዝግጅት የተናገሩት የጋዜጠኛው ወንድም አቶ ታሪኩ ደሳለኝ በወቅቱ የጨጓራና የወገብ ህመም እንዳሰቃየው ገልጾልናል ብለዋል፡፡

ይሁን እንጂ ሰሞኑን በድጋሚ ልንጠይቀው ስንሞክር በማረሚያ ቤቱ አትችሉም ተባልን ያሉት አቶ ታሪኩ ጓደኞቹም ተመሳሳይ እክል እንደገጠማቸው አስረድተዋል፡፡ አሁን ላይ ያለበትን ሁኔታ አናውቅም የተመስገን ደህንነት አስጨንቆናል ሲሉም ነው የገለጹት፡፡

የሶስት አመት እስራት ተፈርዶበት በዝዋይ ማረሚያ ቤት የሚገኘው ተመስገን ደሳለኝ ከዚህ ቀደም ህክምና መከልከሉ ሲዘገብ ቆይቷል፡፡ በኋላ ላይ ግን ተመስገን ህክምና ማግኘቱ የተነገረ ሲሆን ይህንኑ የጤና ሁኔታውን ለመከታተል እንድንጎበኘው ይፈቀድልን በማለታችን ተከለከልን ሲሉ ነው የተመስገን ቤተሰቦችና ወዳጆች መናገራቸው የተዘገበው፡፡ ጋዜጠኛው ከእስር ለመፈታት ቢያንስ 10 ወራት እንደሚቀረው ነው የተናገሩት፡፡

በስም ማጥፋት፣ ሕዝብን በማነሳሳትና ሀሰተኛ መረጃን በማሰራጨት ክስ የሦስት ዓመት እስራት የተፈረደበትን ጋዜጠኛ እስራት የመብት ድርጅቶች ሲያወግዙና ጋዜጠኛው እንዲፈታ ሲጠይቁ መቆየታቸው ይታወሳል።

ተመስገን ከዚህ ቀደም በእስር ላይ የሕክምና አገልግሎት ተከልክሎ እንደነበር የጋዜጠኛ ተሟጋች ቡድኑ/CPJ/ በተደጋጋሚ መዝግቧል።voanews
Related story: Where Is Jailed Journalist Temesgen Desalegn?

READ  ኢትዮጵያ በ 2025 ባለመካከለኛ ገቢ ሀገር አትሆንም ተባለ

It is “unacceptable” that the government was unwilling or unable to provide Temesgen Desalegn’s relatives with information after two years of detention.

ADDIS ABABA, Ethiopia (Associated Press)— Human rights groups are asking Ethiopia’s government to immediately disclose the whereabouts of a popular local journalist who has been behind bars since October 2014.

The Association for Human Rights in Ethiopia and DefendDefenders on Wednesday called it “unacceptable” that the government was unwilling or unable to provide Temesgen Desalegn’s relatives with information after two years of detention.

The groups say Temesgen was jailed on “spurious charges.” The journalist is serving a three-year sentence on charges of defamation, incitement and false publication.

The public relations head of the Ethiopian Federal Prison Administration, Gizachew Mengiste, tells The Associated Press he has no information about Temesgen’s whereabouts
Ethiopia declared a state of emergency in October amid massive anti-government protests, leading to the arrest of at least two journalists.
Source: The Washington Post

NO COMMENTS