የቄጤማ ሰልባጅ በጨርቆስ

0
153
የስልሳ አመቷ ሰልባጅ ቄጤማ ሻጭ በጨርቆስ
በከተማችን አዲስ አበባ አስገራሚ እና ሊታመኑ የማይችሉ ተግባራት ሲከናወኑ ይሰማል ይታያል፡፡ ይሸጣሉ ተብለው የማይታሰቡ እና የማይገመቱ ቁሶች ዋጋ ወጥቶላቸው ሲሸጡ ሲለወጡ ሲገዙ ይታያል፡፡
  • የስልሳ አመቷ ሰልባጅ ቄጤማ ሻጭ በጨርቆስ

በከተማችን አዲስ አበባ  አስገራሚ እና ሊታመኑ የማይችሉ ተግባራት ሲከናወኑ ይሰማል ይታያል፡፡ ይሸጣሉ ተብለው የማይታሰቡ እና የማይገመቱ ቁሶች ዋጋ ወጥቶላቸው ሲሸጡ ሲለወጡ ሲገዙ ይታያል፡፡

ይህ መሰሉ አስገራሚ ንግድ በአብዛኛው በመርካቶ ምናለሽ ተራ የሚከወን ሲሆን ከወደ ጨርቆስ የተሰማው የሰልባጅ ቄጤማ ሽያጭ ዜና አስገራሚ ሆኗል፡፡

ጉዳዩ እንደዚህ ነው ፡፡ ሰዎች ገና ተቆርጦ ‹‹በአዲስነቱ›› ለገበያ የቀረበ ቄጤማ ገዝተው አገልግሎቱ ሲያበቃ ከቆሻሻ ቆጥረው ይጥሉታል፡፡

ለስልሳ አመቷ ሰልባጅ ቄጤማ ሻጭ ግን ሰው ጎዝጉዞ ቆሻሻ ነው ብሎ የጣለው ቄጤማ እሳቸውን እና ሌሎች ሶስት የቤተሰብ አባላትን የሚያስተዳድር ለመሆን በቅቷዋል፡፡

በሰዎች አገልግሏል ተብሎ የተጣለው ቄጤማ ከታጠበ በኋላ በአዲስነቱ ከሚሸጥበት ግማሽ በታች ዋጋ ተቆርጦለት በጨርቆስ ገበያ ለገበያተኛ በግልጽ ይቀርባል፡፡

በሸገር ሬድዮ ጣቢያ በተላለፈው በዚሁ ወሬም የሰልባጅ ቄጤማው ደንበኛ የሆኑ ሰዎችንም አስተያየት አቅርቧል፡፡

በጨርቆስ ሲሳይ ሜዳ ተብሎ በሚታወቀው አካባቢ የሚሸጠው ሰልባጅ ቄጤማ ሻጭና ገዢ ሳይወሻሹ እና ሳይደባበቁ ቄጤማው አገልግሎቱን ከጨረሰ በኋላ ዳግም እጥብት ተደርጎለት ለሽያጭ እንደሚውል እውቅና ተሰጥቶት ለገበያ ይቀርባል፡፡

የሬድዮ ጣቢያው ጋዜጠኛ ዘገባውን የጨረሰው በዚህ አጭር ግጥም ነበር

‹‹አቅም ላጣ ለቸገረው

ለቔጤማም ሰልባጅ አለው››

READ  በዚምባብዌ የታሰሩ 34 ኢትዮጵያዉያን ክስ ተመሰረተባቸው ተባለ

NO COMMENTS