በግንባሩ ላይ የቀድሞውን የኢትዮጵያ ካርታ ይዞ ተወለደው አስገራሚ ህጻን ‹‹ሚስተር ኢትዮጵያ››

0
224

ከኢትዮጵያዊት እናቱ እና ከጣሊያናዊ አባቱ የተወለደው ዜኖ የተባለው ህጻን ግንባሩ ላይ የኤርትራ ምድርን ያካተተውን የቀድሞውን የኢትዮጵያ ካርታ በግንባሩ ላይ ታትሞ ተወልዷል፡፡

እ.ኤ.አ በ2002 በ17 ዓመቷ ሚስ አፍሪካ የተባለችው እና የዚህ አስገራሚ ህጻን ወላጅ እናት የሆነችው ሞዴል እና ተዋናይት ትዝታ አብርሃም ገና በአምስት አመቷ ነበር ወደ ጣሊያን የተጓዘችው የሚለን የአዲስ ቴሌቪዥን ዘገባ እሷን እና ወላጅ እናቷን ቃለ መጠይቅ በማድረግ ይህንን አስገራሚ ዘገባ ይዞ ወጥቷል፡፡

ይህቺው ኢትዮጵያዊት ጣሊያናዊ ዜግነት ያለው የትዳር አጋር ያላት ሲሆን በ30 ዓመቷ ነበር ይህን አስገራሚ ህጻን ለመጸነስ የበቃችው፡፡

እናት በእርግዝናዋ ግዜ ኢትዮጵያን ትናፍቅ እንደነበር ያተተው ዘገባው ህጻኑ ሲወለድ በግንባሩ ላይ ‹‹ሽታ›› በሚባለው የተለየ ቀለም ግንባሩ ላይ የኢትዮጵያ ካርታን አትሞ ወጥቷል፡፡

እናት ስለጉዳዩ ስትናገር ዜኖ ወይም ‹‹ሚስተር ኢትዮጵያ›› ከተወለደ ከ 10 ቀናት በኋላ ግንባሩ ላይ የታተመው የቀድሞው የኢትዮጵያ ካርታ በጉልህ እየታየ መጣ ትላለች፡፡

በእርግዝናዬ ወራት ኢትዮጵያ በጣም ትናፍቀኝ ነበር የምትለው የዜኖ እናት ህጻኑ ሲወለድ በአጋጣሚ የኢትዮጵያን የቀድሞ ካርታ በግንባሩ ላይ መስፈሩን ታስረዳለች፡፡

ህጻኑ ሲያድግ የካርታው ምስል በህይወት ዘመኑ ሙሉ ቢቆይለት ደስተኛ መሆኗንም ወላጅ እናቱ ተናግራለች፡፡

የህጻኑ አያትም በጉዳዩ መገረማቸውን እና መጀመሪያ ሲያዩት ወድቆ የተጎዳ እንደመሰላቸው እና በኋላ ላይ ግን በግንባሩ ላይ ያለው ምስል የቀድሞው የኢትዮጵያ ካርታ መሆኑን መገንዘባቸውን ለፕሮግራሙ አዘጋጅ ነግረውታል፡፡

በተለምዶ ‹‹ሽታ›› እየተባለ የሚጠራው እና ነፍሰ ጡር ሴት በእርግዝናዋ ወራት ያማራትን ነገር ሳታገኝ ስትቀር በህጻኑ የተለያዩ የሰውነት ክፍሎች ላይ ጠቆር አሊያም ቀላ ያለ ምልክት ይወጣል የሚል እሳቤ በማህበረሰባችን ውስጥ በሰፊ የሚታመንበት ቢሆንም በህክምና ባለሞያዎች የተረጋገጠ እንዳልሆነ ይታወቃል፡፡

READ  ‹‹ትክክለኛ የእየሱስ ክርስቶስ ምስል ›› ተገኘ መባሉ ብዙዎችን እያወዛገበ ይገኛል

 

NO COMMENTS