የሜቄዶንያ መስራች ወጣት ቢንያም ‹‹በሽታ ሃብት ነው›› ይለናል

0
181
  • ስለጤንነቱ ማረጋገጫ ሰጥቷል

ሜቄዲንያ የአረጋውያን እና የአእምሮ ህሙማን መርጃ ማእከል መስራች የሆነው ወጣት ቢንያም ‹‹ታሟል›› የሚል ወሬ መናፈሱን ተከትሎ የታዲያስ አዲስ የሬድዮ ፕሮግራም ባልደረቦች ከወጣቱ ግብረሰናይ ጋር ቆይታ አድርገው ነበር፡፡

ቢንያም አልፎ አልፎ ከሚያመው መጠነኛ የጉሮሮ ህመም የተለየ እና ለአደጋ የሚያጋልጥ ህመም እንዳልገጠመው የተናገረ ሲሆን ለበሽታም ብዙዎቻችን ከምንረዳው አረዳድ የተለየ አስተያየን ሰጥቷል፡፡

በታዲያስ አዲስ የሬድዮ ፕሮግራም አዘጋጆች ‹‹ያንተ መኖር የብዙዎች ተስፋ›› በመሆኑ እና ብዙዎችም ላንተ ስለሚጨነቁ እንዲሁም አንተ ለራስህም ቦታ ስለማትሰጥ ለአንተ ከማሰብ ነው መሰል ወሬዎች የመጡት የሚል አስተያየት የተሰነዘረለት ወጣሉ ግብረሰናይ ስለ በሽታ በሰጠው አስተያየት እርሱ በሚከተለው የክርስትና ሃይማኖት ‹‹በሽታ ሃብት ›› ስለመሆኑ አስረድቷል፡፡

በእርግጥ በሽታ ‹‹ለተግሳጽም ›› መኖሩን አስረድቶ ‹‹በሽታ ሃብት ነው›› ያለበትን የመጽሃፍ ቅዱስ የእዮብን ታሪክንም አንስቷል፡፡ በሽታ የጽናትና የታማንነት ማሳያ ሊሆን እንደሚችል በመጥቀስ፡፡

Interview on Tadias Addis

ከስጋዊ በሽታ መንፈሳዊ በሽታ፤ ከዓለማዊ ድህነትም መንፈሳዊ ድህነት የበለጠ አስከፊ እና አስፈሪ እንደሆነ እና ሁላችንም ታመን ልንሞት የምንችል በመሆኑ ‹‹በሽታ ብዙ የሚያስጨንቅ አይደለም›› ሲል እጅግ አስገራሚ አስተያየቱን ሰጥቷል፡፡

የእርዳታ ስራውን በተመለከተም የአዲስ አበባ ከተማ እሰተዳደር በሰጣቸው መሬት ላይ ግንባታ እያከናወኑ ስለመሆኑ እና የተረጂዎች ቁጥርም ወደ 1500 መድረሱን እንዲሁም ለመጪው ገና ህብረተሰቡ በዓሉን ከተረጂዎች ጋር እንዲያሳልፍ የሚረዳው ነገር እንኳን ባይኖረው ወደ ማዕከላቸው በመምጣት አረጋውያኑን እና

የአእምሮ ህሙማኑን እንዲጎበኙ ጥሪውን አቅርቧል፡፡

ይህ የገና በዓል ፕሮግራምም በአዲሱ ማእከል ማለትም አያት ኮንዶሚኒየም አጠገብ ፍሉሃ መድሃኒአልም ፊት ለፊት የሚከናወን መሆኑንም ጠቁሟል፡፡

READ  ትውልደ ኢትዮጵያዊቷ ብሔራዊ ባንክንና የፋይናንስ ድርጅቶችን ከሰሱ

NO COMMENTS