ለ 31 አመታት ባልፈጸመው ወንጀል በእስር የቆየው አሜሪካዊ ግለሰብ የ 37 ዶላር ካሳ ተሰጠው መባሉ እያነጋገረ ነው

0
5825
ለ 31 አመታት በእስር የማቀቀው ማኪኒ
ለ 31 አመታት ባልፈጸመው ወንጀል በእስር የቆየው አሜሪካዊ ግለሰብ የ 37 ዶላር ካሳ ተሰጠው

ለ 31 አመታት ባልፈጸመው ወንጀል በእስር የቆየው አሜሪካዊ ግለሰብ የ 37 ዶላር ካሳ ተሰጠው መባሉ እያነጋገረ ነው
ይህን ተከትሎ ግለሰቡ የ 1 ሚሊዮን ዶላር ካሳ መጠየቁ ተነግሯል

በአውሮፓዊያኑ 1977 በአሜሪካ ቴኒሲ አንዲት እንስት በሁለት ግለሰቦች አሰቃቂ የመደፈር ወንጀል ይፈጸምባታል፡፡ ይሁን እንጂ ሴትየዋ ጎረቤቷ የነበረውን ሎውረንስ ማኪኒን ተጠያቂ በማድረጓ የ 22 አመት ጎረምሳ የነበረው ይህ ሰው በመድፈርና በዘረፋ ወንጀሎች ተከሶ በ 1988 ዓ/ም የ 115 አመታት እስር ተፈርዶበት ወደ ወህኒ ይወረወራል፡፡

ባልፈጸመው ወንጀል ለ 31 አመታት በእስር የማቀቀው ማኪኒ በ 2008 ላይ ወንጀሉ ዳግም ሲታይ በ ዲኤንኤ ምርመራ ከወንጀሉ ንጹህ መሆኑ ይረጋገጣል፡፡ የፍርድ ሂደቱ ዳግም ታይቶም በቀጣዩ አመት ከእስር ይፈታል፡፡ የ 53 አመት አዛውንት ሆኖ ከእስር የተለቀቀው ግለሰቡ በግዛቱ የፍትህ አስተዳደር ህይወትህን ለመቀጠል እንድትችል ተብሎ የተሰጠው ካሳ ግን 37 ዶላር እንደነበር ነው አፍሪካን አብዴት የዜና ምንጭ ታሪኩን ያስታወሰው፡፡

አሁን ላይ የ 61 አመት አዛውንት የሆነው ግለሰቡ ጉዳዩ ዳግም እንዲታይለት ለቴኒሲ አስተዳደር ጥያቄ እቀረበ መሆኑ ተነግሯል፡፡ ይህ የግለሰቡ ጥያቄ ደግሞ የ 1 ሚሊዮን ዶላር ካሳ ይሰጠኝ የሚል መሆኑን የተናገረው ዘገባው ይሁን እንጂ ባለፈው መስከረም ላይ የግዛቱ ባለስልጣናት ጥያቄውን ውድቅ ማድረጋቸው ተገልጿል፡፡

የሰውየው ጉዳይ አሁን ላይ ዳግም መነጋገሪያን መፍጠሩ እየተዘገበ ይገኛል፡፡ ሲኤንኤንን ጨምሮ በርካታ መገናኛ ብዙሀን በሀገሪቱ የፍትህ ስርአት ላይ ጥያቄ የሚያስነሳውን ይህን ጉዳይ በሚመለከት እየዘገቡ የሚገኝ ሲሆን ባላጠፋው ነገር በርካታ እድሜውን በእስር ሲማቅቅ ላሳለፈውና ከስድብ የሚቆጠር መናኛ ካሳ ለተከፈለው ሰው ሀዘን የሚገልጹ መበርከታቸው ተነግሯል፡፡

READ  የፊሊፒንሱ ፕሬዘዳንት ሮድሪጎ ዱቴርቴ ሙሰኛ ባለስልጣናትን ከሄሊኮፕተር ላይ እወረውራለሁ አሉ

Read More: MAN RECEIVES $75 CHECK TO RESTART HIS LIFE AFTER BEING WRONGLY IMPRISONED FOR 31 YEARS

A man from Tennessee, Lawrence McKinney, who was wrongly imprisoned for 31 years for a crime he didn’t commit has asked for a $1m compensation to restart his life after he was handed $75 by the Tennessee Department of Corrections.

In October 1977, a woman was raped by two strangers and upon questioning by police, identified one of her alleged rapist as her neighbor, Lawrence- he was then convicted on rape and burglary charges in 1978 and sentenced to 115 years in jail at the young age of 22.
In 2008, DNA evidence cleared Lawrence of any crimes and he was now released from prison the following year, but was sadly given $75 to start his life from scratch.africaupdates

NO COMMENTS