ኢትዮጵያ በ 2025 ባለመካከለኛ ገቢ ሀገር አትሆንም ተባለ

0
4015
ኢትዮጵያን በ 2025
የሀገሪቱ የነፍስ ወከፍ ገቢና የሰብአዊ እድገት ደረጃ የሚጠበቀውን ያክል እድገት አለማስመዝገቡ ለእቅዱ አለመሳካት ምክንያት ተብሏል

የሀገሪቱ የነፍስ ወከፍ ገቢና የሰብአዊ እድገት ደረጃ የሚጠበቀውን ያክል እድገት አለማስመዝገቡ ለእቅዱ አለመሳካት ምክንያት ተብሏል

የተባበሩት መንግስታት የንግድና የልማት ድርጅት /UNCTAD/ በአዲስ ሪፖርቱ ኢትዮጵያ በፈረንጆቹ 2025 ላይ ባለመካከለኛ ገቢ ሀገር እሆናለሁ ብላ የያዘችው እቅድ እንደማይሳካ አስታወቀ፡፡ ድርጅቱ የአለም ደሀ ሀገራት የ 2016 የኢኮኖሚ ሪፖርትን ይፋ ሲያደርግ ኢትዮጵያን በ 2025 መካከለኛ ገቢ ያላቸው ሀገራት ይሆናሉ ብሎ ከዘረዘራቸው ሀገራት ተርታ ሰርዟታል፡፡

የአለም ባንክና የኢትዮጵያ መንግስት ዘንድሮም ኢትዮጵያ የ 8 በመቶ ከፍተኛ የምጣኔ ሀብት እድገት እንዳስመዘገበች ሲናገሩ መቆየታቸውን የእንግሊዘኛው ፎርቹን በዘገባው አስታውሷል፡፡

የድርጅቱ ሪፖርት እንዳለው ከሆነ የኢትዮጵያ የነፍስ ወከፍ ገቢና የሰብአዊ እድገት ደረጃ የሚጠበቀውን ክል እድገት አለማስመዝገቡ ለሀገሪቱ የኢኮኖሚ ደረጃ ለውጥ እንቅፋት ይሆናል ተብሏል፡፡ የነፍስ ወከፍ ገቢ በኢትዮጵያ ባለፉት አምስት አመታት በእጥፍ አድጎ 794 ዶላር ደርሷል፡፡ ሀገሪቱ በሰብአዊ እድገት ሰንጠረዥ ላይ በ 173ኛ ደረጃ ላይ ሰፍራለች የሚለው ሪፖርቱ ይህ ውጤትም የኢኮኖሚ ሀሽግግር እንድታደርግ የሚያስችላት እንዳልሆነ ነው የተነበየው፡፡

ድርጅቱ በሪፖርቱ 13 ታዳጊ ሀገራት ወደ ባለመካከለኛ ኢኮኖሚ ይሸጋገራሉ ሲል የተነበየ ሲሆን ይሁን እንጂ ከአፍሪካ አህጉር እንደ ኢኳቶሪያል ጊኒና አንጎላን የመሳሰሉ ሀገራት ካልሆኑ በቀር ኢትዮጵያ ያቀደችውን ግብ አታሳካም ብሏል፡፡ በመላው አለም 48 እጅግ ደሀ ሀገራት ይገኛሉ የሚለው ድርጅቱ በነዚህ ሀገራት ያለው ድህነት ባለፉት ሶስት አመታት በእጥፍ አድጓል፡፡

ድርጅቱ የዛሬ 45 አመት ይህን አመታዊ ሪፖርት ይፋ ማድረግ ከጀመረ ወዲህ ባሉት አመታትም 5 ሀገራት ብቻ ናቸው ከድህነት ወደ ባለመካከለኛ ኢኮኖሚ ሀገርነት የተሸጋገሩት ሲል ይፋ አድርጓል፡፡

READ  ተመሳሳይ መድኃኒቶች በተለያየ ሰው ሲወሰዱ ፈዋሽነታቸው እኩል አለመሆኑ ተገለጸ

የኢትዮጵያ መንግስት የአስከፊ ድህነት አሀዝን ወደ 30 በመቶ መቀነሱን የሚናገር ሲሆን በ 2025 ሀገሪቱን ባለመካከለኛ ኢኮኖሚ አደርጋለሁ የሚል እቅድም ነበረው፡፡ መንግስት ሀገሪቱ በፈጣን ሁኔታ እያደገች መሆኗን የሚናገር ሲሆን ይህንንም አለም አቀፍ ድርጅቶች ሲመሰክሩለት ይሰማል፡፡ ይሁን እንጂ አዲሱ የተመድ ሪፖርት ሀገሪቱ የተባለው ደረጃ ላይ ለመድረስ ገና ብዙ እንደሚቀራት ነው ያረጋገጠው፡፡allafrica

NO COMMENTS