የጥርኝን ምርት ማሳደግ የሚያስችል ምርምር እያካሄደ መሆኑን የአዲስ አበባ ዩኒቨርሲቲ አስታወቀ

0
633
የጥርኝን ምርት
በሳይንሳዊ መጠሪያው ማስክ የተሰኘው የጥርኝ ተዋፅኦ በዓለም የሽቶ ኢንዱስትሪ ገበያ እጅግ ተፈላጊ ሲሆን፤ ለኢንዱስትሪዎች የጥርኝ ምርት ከሚልኩ አገራት መካከል አንዷ ኢትዮጵያ ናት።

 

በሳይንሳዊ መጠሪያው ማስክ የተሰኘው የጥርኝ ተዋፅኦ በዓለም የሽቶ ኢንዱስትሪ ገበያ እጅግ ተፈላጊ ሲሆን፤ ለኢንዱስትሪዎች የጥርኝ ምርት ከሚልኩ አገራት መካከል አንዷ ኢትዮጵያ ናት።

በአዲስ አበባ ዩኒቨርሲቲ የተፈጥሮ ሳይንስ ኮሌጅ ስነ መካነ አራዊት ትምህርት ክፍል ተመራማሪ ፕሮፈሰር አፈወርቅ በቀለ እንደገለጹት በደቡብና ምዕራብ ኢትዮጵያ ቁጥራቸው 200 የሚደርሱ አርሶ አደሮች ጥርኝን በባህላዊ መንገድ በመሰብሰብ ስራ ተሰማርተዋል።

ከአርሶ አደሮቹ ባህላዊ አሰባሰባቸው ባሻገር ህገ ወጥ ደላሎች ምርቱን በአነስተኛ ገንዘብ ገዝተው ባእድ ነገር በመቀላቀል የአካባቢውን ማህበረሰብ ጥቅም በከፍተኛ ሁናቴ ይጎዱታል።

ስለሆነም የጥርኝን ተፈላጊነትና የአርሶ አደሩን ተጠቃሚነት ከግምት በማስገባት ዩኒቨርሲቲው የተሻሻለ የጥርኝ አሰባሰብ ተግባራዊ ማድረግ ከተሰማራባቸው የምርምር መስኮች አንዱ እንደሆነ ፕሮፌሰር አፈወርቅ ገልጸዋል።

ምርምሩ የሚካሄደው በጫካ የሚደረግ የጥርኝ አያያዝ ዝርያውን የመቀነስ ተዕፅኖ ስለሚኖረው የተሻለ የወጥመድ ስልት በመጠቀም እንስሳውን በቤተ ሙከራ ለማራባትና ማህበረሰቡ ተጠቃሚ የሚሆንበትን እድል ለመፍጠር ነው።

“በአያያዝ ቴክኒክ፣ በአመጋገብና የተሻለ ምርት እንዴት ማግኘት እንደሚቻል ከዚህ ቀደም የተጠና ሲሆን፤ በአሁኑ ወቅት ተጨማሪ ፕሮጀክት በመንደፍ ገንዘብ ተለቆልን ጥርኝን በዘመናዊ መንገድ ለማርባት እየተንቀሳቀስን ነው” ብለዋል ፕሮፌሰሩ።

በመሆኑም ህገ ወጥ ደላሎችን በመከላከልና ዘመናዊ አረባብ በመከተል ህብረተሰቡን ተጠቃሚ ከማድረግ ባሻገር የጥርኝን አጠቃቀም ከባህላዊ ወደ ዘመናዊ ማሸጋገሩ አገሪቷ ወደ ውጭ የምትልከውን የጥርኝ ምርት መጠን እንደሚያሳድገው አብራርተዋል።

ጥርኝን ለሽቶ ኢንዱስትሪያቸው በሰፊው ከሚጠቀሙ አገራት መካከል ፈረንሳይና ቻይና ተጠቃሽ ናቸው። ena

READ  የትምህርት መማሪያ መጽሐፍት ብላክ ማርኬት ህጋዊነት

NO COMMENTS