የግልገል ጊቤ ሶስት የሀይል ማመንጫ ዛሬ ይመረቃል

0
11539
የግልገል ጊቤ ሶስት የሀይል ማመንጫ
1.8 ቢሊዮን ዶላር በጀት የጠየቀውና ዘጠኝ አመታትን ያስቆጠረው ግልገል ጊቤ ሶስት የሀይል አውታር ካለፈው አመት ጀምሮ በከፊል ሀይል ሲያመነጭ ቆይቷል፡፡

1.8 ቢሊዮን ዶላር በጀት ገየጠየቀውና ዘጠኝ አመታትን ያስቆጠረው ግልገል ጊቤ ሶስት የሀይል አውታር ካለፈው አመት ጀምሮ በከፊል ሀይል ሲያመነጭ ቆይቷል፡፡ ይህ የሀይል ማመንጫ አጠቃላይ የማመንጨት አቅሙ 1870 ሜጋ ዋት መሆኑን የተናገረው የአፍሪካን ቢዝነስ ኮሙኒቲ ዘገባ ካለፈው አመት ጀምሮ እስከ 900 ሜጋ ዋት ሲያመነጭ መቆየቱን ተናግሯል፡፡

ጊቤ ሶስት በኦሞ ወንዝ ላይ የተገነባ ሶስተኛው የሀይል ማመንጫ ሲሆን ከዚህ ቀደም ጊቤ አንድና ጊቤ ሁለት በዚሁ ወንዝ ላይ መገንባታቸው ይታወቃል፡፡ ጊቤ ሶስት የሀገሪቱን አጠቃላይ የሀይል አቅርቦት ወደ 4,200 ሜጋ ዋት ያሳድገዋል ተብሎ ይጠበቃል፡፡ የጊቤ ሶስት ግድብ ታላቁ የህዳሴ ግድብ ስራ እስኪጀምር ለሀገሪቱ ትልቁ የሀይል ማመንጫ አውታር ሆኖ እንደሚቆይ ዘገባው ተናግሯል፡፡

የዚህ ትልቅ የሀይል ማመንጫ ፕሮጀክት 40 ከመቶ ወጪ ከመንግስት በኩል ሲሸፈን ቀሪው 60 በመቶ ደግሞ ከቻይና ኤግዚም ባንክ በተገኘ ብድር መሸፈኑ ተነግሯል፡፡ የግድቡን ግንባታም ሳሊኒ የተባለው የጣሊያን ኩባንያ እንዳካሄደው ተነግሯል፡፡ ቁመቱ 820 በሆነ የኮንክሪት ሙሌት መገንባቱ ተነግሯል፡፡ ሀገሪቱ በዚሁ ተፋሰስ ላይ ጊቤ አራትና ጊቤ አምስት የተባሉ ፕሮጀክቶችን ለመገንባት እቅድ እንዳላትም ተነግሯል፡፡ africabusinesscommunities

READ  አካል ጉዳተኞች በቀላል ባቡር ትራንስፖርት መጠቀም አልቻሉም

NO COMMENTS