ደብዛው ጠፍቶ የሰነበተው እና በእስር ላይ የሚገኘው ጋዜጠኛ ተመስገን ደሳለኝ በዝዋይ ማረሚያ ቤት እንዳገኙት ቤተሰቦቹ አስታወቁ

0
7905
ብሞትም እንዲቀብረኝ ልጄን ቢለቁልኝ ደስ ይለኛል
“ብሞትም እንዲቀብረኝ ልጄን ቢለቁልኝ ደስ ይለኛል” ሲሉ የጋዜጠኛ ተመስገን ደሳለኝ እናት ተማጠኑ።

 

ደብዛው ጠፍቶ የሰነበተው እና በእስር ላይ የሚገኘው ጋዜጠኛ ተመስገን ደሳለኝ በዝዋይ ማረሚያ ቤት እንዳገኙት ቤተሰቦቹ አስታወቁ “ብሞትም እንዲቀብረኝ ልጄን ቢለቁልኝ ደስ ይለኛል” ሲሉ የጋዜጠኛ ተመስገን ደሳለኝ እናት ተማጠኑ።

ላለፉት ዘጠኝ ቀናት ታስሮ ይገኝበታል በተባለው ዝዋይ እስር ቤት እንዳጡት ሲገልጹ የቆዩት ቤተሰቦቹ በትላንትናው ዕለት በአስረኛ ቀኑ እንዳገኙትና ለአምስት ደቂቃ እንዳዩት ለአሜሪካ ድምፅ ገለጹ። እናቱ ወ/ሮ ፋናዬ ይርዳው ታማሚ መሆናቸውን ገልፀው የእስር ጊዜውን ስለጨረሰ በአመክሮ እንዲፈታላቸው ጠይቀዋል።

ጋዜጠኛ ተመስገን ደሳለኝ የፍትህ ጋዜጣ፣ የአዲስ ታይምስና የፋክት መጽሔት ባለቤት እና አዘጋጅ በነበረበት ወቅት በጹሑፍ ሥራዎቹ “በሀሰት ወሬ መንዛት” በሚል ክስ ቀርቦበትና “ጥፋተኛ” ተብሎ የተፈረደበትን የሦስት ዓመት እስራት ለመጨረስ በዝዋይ ማረሚያ ቤት ይገኛል። በዚህ ማረሚያ ቤት ከታሰረ ሁለት ዓመት ከሦስት ወር እንዳስቆጠረ ቤተሰቦቹ ይናገራሉ። የጋዜጠኛ ተመስገን ደሳለኝ ወንደም አላምረው ደሳለኝ ለአሜሪካ ድምፅ እንደተናገረው፤ በዛሬው ዕለት ዝዋይ እስር ቤት ወንድሙን ፍለጋ የሄደው ለመሞከር እንጂ አገኘዋለሁ በሚል ተስፋ አልነበረም።

የጋዜጠኛ ተመስገን ደሳለኝ ይዞታ ላለፉት 10 ቀናት ደብዛው ጠፍቶ የሰነበተው እና በእስር ላይ የሚገኘው ጋዜጠኛ ተመስገን ደሳለኝ በዝዋይ ማረሚያ ቤት እንዳገኙት ቤተሰቦቹ አስታወቁ፡፡ ቤተሰቦቹ “ተመስገን ዝዋይ የለንም ተብለናል” ሲሉ አቤቱቻቸውን ለተለያዩ አካላት ሲያቀርቡ ሰንብተዋል፡፡

ትላንት ለጥቂት ደቂቃዎች ተመስገንን መመልከት እንደቻሉና ጤንነቱ መቃወሱን ተናግረዋል፡፡ በጻፋቸው እና ባሳተማቸው ጽሁፎች ክስ ቀርቦበት እና ተፈርዶበት ዝዋይ ማረሚያ ቤት እስሩን እየገፋ ይገኝ የነበረው የጋዜጠኛ ተመስገን ደሳለኝ ደብዛ መጥፋት የሰሞኑ መነጋገሪያ ሆኖ ነዉ የሰነበተዉ፡፡

READ  “ተመስገን ሕመሙ ፀንቶበታል” የጋዜጠኛ ተመስገን ደሳለኝ ቤተሰቦች

ከሰብዓዊ መብት ተቋማት እስከ ጋዜጠኛ መብት ተከራካሪ ድርጅቶች ለጉዳዩ አጽንኦት ሰጥተው መግለጫ እስከ ማውጣት እና በማኅበራዊ መገናኛዎች ዘመቻ እስከመክፈት ደርሰዋል ፡፡

የተመስገን ደሳለኝ ቤተሰቦች በዝዋይ ማረሚያ ቤት “ተመስገን እዚህ የለም” ተብለናል ካሉበት ቀን አንስቶ በፌደራል ማረሚያ ቤቶች አስተዳደር ስር ባሉ የተለያዩ እስር ቤቶች ጋዜጠኛውን ሲያፈላልጉ ቆይተዋል፡፡

ወደ ዝዋይ ማረሚያ ቤትም በየቀኑ በመሄድ ጥያቄቸውን በተደጋጋሚ አቅርበዋል፡፡ እስከ ትላንት ረፋድ ድረስ ግን ያገኙት የነበረው ተመሳሳይ ምላሽ “የለም” እንደነበር ሲገልጹ ነበር፡፡

ትላንት ዓርብ ታሕሳስ 7 ከአዲስ አበባ ወደ ዝዋይ ተጉዞ የነበረው ወንድሙ አላምረው ደሳለኝ ግን አምስት ደቂቃ ላልሞላ ጊዜ ተመስገንን አግኝቶት እንደነበር ለዶይቸ ቨለ ገልጿል፡፡

ወንድሙን እንዴት ለማየት እንደተፈቀደለት በዝርዝር ያስረዳል፡፡ “ከበር ላይ ጠብቅ ቆይ ተባልኩኝ፡፡ ገባን፣ አስጠሩት፣ ጠየቅን፡፡ ከሶስት ደቂቃ እንኳ ያልበለጠ ነው፡፡ ምንም ነገር ያወራነው የለም፡፡ ሰላምታ ተለዋወጥን፡ ‘ጤንነትህን ስለው?’ ‘ጨጓራዬን በጣም እያመመኝ ነው’ ያለው፡፡ ሌላው በሽታም እንዳለ ነው- ወገቡም፣ ጆሮውም፡፡ ‘ሌላውን ምን ትጠይቀኛለህ?’ ነው ያለኝ፡፡ ‘ጆሮዬንም ያመኛል፤ ህክምና የለም፤ ግን ጨጓራዬን አሁን በጣም እያመመኝ ነው’ አለ፡፡

ዓለም አቀፉን የጋዜጠኞች መብት ተከራካሪ ድርጅት (ሲፒጄን) ጨምሮ ሌሎች የሰብዓዊ መብት ተቋማት ጋዜጠኛው ሀሳቡን በነጻነት በመግለጹ ምክንያት መታሰር እንደሌለበት ሲያሳስቡ ቆይተዋል፡፡VOA Amharic

NO COMMENTS