የዶክተሮች ዓመት-ከምሁራን እፍ ያለው አዲሱ የፓለቲካችን ፍቅር

0
794
ጥልቅ ተሃድሶ ላይ ነን
ሰሞኑን ጥልቅ ተሃድሶ ላይ ነን፡፡ ጠቅላይ ሚኒስትሩ ወቅታዊውን የሀገራችንን ችግር ለመፍታት አንድ እርምጃ ነው ያሉትን የመንግስት አስፈጻሚ አካላት ዳግም የማዋቀር ስራ አስፈላጊ ነው ብለው ለህዝብ ገለጹ፡፡ ከዚያም የራሳቸውን ካቢኔ ዳግም አደራጁ፡፡

የዶክተሮች ዓመት-ከምሁራን እፍ ያለው አዲሱ የፓለቲካችን ፍቅር፤
(ከስናፍቅሽ አዲስ)
ሰሞኑን ጥልቅ ተሃድሶ ላይ ነን፡፡ ጠቅላይ ሚኒስትሩ ወቅታዊውን የሀገራችንን ችግር ለመፍታት አንድ እርምጃ ነው ያሉትን የመንግስት አስፈጻሚ አካላት ዳግም የማዋቀር ስራ አስፈላጊ ነው ብለው ለህዝብ ገለጹ፡፡ ከዚያም የራሳቸውን ካቢኔ ዳግም አደራጁ፡፡ ካደራጁ በኋላ ክልሎችም ግምገማቸውን ተከትሎ አዳዲስ የካቢኔ መዋቅራቸውን ዳግም ለማደራጀት በቅተዋል፡፡የፌዴራሉ ካቢኔ ድንገት በምሁራን ተሞላ መባሉ የቀድሞዎችን አመራሮች ስሜት የሚጎዳ ግርግር ይመስለኛል፡፡

ከሃያ አምስት ዓመት ቆይታ በኋላ ደርሶ ከዚህ በኋላ ብቃት ባለው የተማረ የሰው ሃይል የተዋቀረ አስፈጻሚ ነው ብሎ ማቀንቀኑ ለዓመታት ድርጅቱን በጫንቃቸው እዚህ ያደረሱ ነባር አመራሮችን ያለ ብቃታቸው በወንበሩ ላይ የኖሩ ብሎ መዝለፍ ይመስለኛል፡፡ እየሆነ ያለው ይሄው ነውና እዚሁ ላይ እናውራ፡፡

አማራ እና ደቡብም የክልል ካቢኔያቸውን ይፋ አድርገዋል፡፡ ትግራይም በተመሳሳይ መልኩ፡፡ ሁሉም እንደ ፌዴራል መንግስቱ ሁሉ እኛም ዶክተር አለን ሲሉ የሰነበቱ ይመስለኛል፡፡ ጥሩ ነው፤ ፖለቲካችን ከምሁራን ጋር አዲስ ፍቅር ውስጥ የገባ መሰለኝና ስጋት ቢጤ ግን ሸነቆጠኝ፡፡
ከዚህ በፊት የነበሩ አመራሮች ከቦታው ጋር ቀጥተኛ ግንኙነት ሳይኖራቸው ዘርፉን ለመምራት መሞከራቸው ውጤቱን ዝቅ እንዲል አድርጎታል የሚለው ግምገማ ጤነኛ ይመስለኛል፡፡ ለሜሪት እና ለእውቀት ትኩረት መሰጠቱም ቢሆን አያስወቅስም፡፡ እንደውም የሀገር ለውጥ የመጀመሪያ ምዕራፍ ነው ብዬ አስባለሁ፡፡ ሜሪትን ዶክተርነት ውስጥ ብቻ መፈለግ ግን ሰርቶ ማፍረስ እንዳይሆንብን ያሳስበኛል፡፡

ፖለቲካውን መምራት፣ ቢሮክራሲውን መካን እና ተቋሙን በብቃት ማራመድ መቻል አንድን ውስን ሙያ ተመራምሮ ለሶስተኛ ዲግሪ ከመብቃት ጋር ብቻ ካገናኘንው አደጋው ይብሳል፡፡

READ  በፈረንሳይ የስደተኞች ጫካ ውስጥ ቁጥራቸው የበዛ ኢትዮጵያዊያን ታግተው እንደሚገኙ ተገለጸ

የምሁራኖቹ መገኛ ዩኒቨርሲቲዎቻችን ናቸው፡፡ አንዳንዱ ዶክተር በትምህርት ጥራት ሳቢያ አበሳውን ከሚያይበት እና ጠዋት ማታ ከሚወቀስበት ስራ ተነስቶ በፖለቲካ ጥራት ሰው ተገምግሞበት ወደማያውቅ ሰላማዊ ህይወት በመምጣቱ ሊደሰት ይችላል፡፡ አንዳንዱ ደግሞ ለምርምር እና ጥናት ተፈጥሮ ለግዜው ስምህ ያስፈልገናል ተብሎ ያለ ክህሎቱ ወደ አመራርነት መጥቶም ይሆናል፡፡

የእኔ ስጋት ከፍ ካደረግናቸው ዶክተሮች ዝቅ ያለ ነገር ከገጠመን እርም ምሁር እንዳንል ነው፡፡ ይሄ ዶክተርን ወደ ወንበር የሚለው ዘመቻ አንድም ጠንካራ የዩኒቨርሲቲ አመራሮቻችንን ብዙም ወደ አልተካኑበት የፖለቲካ ሹመት አምጥቶ ከፍተኛ የትምህርት ተቋማቶቻችንን አደጋ ላይ እንዳይጥል፤ በሌላ በኩል ስሙን ተሸክሞ አቅሙን ያላስፈተሸ ሰነፍ በስሙ ተገን አድርጎ ለራሱ ያልሆነ ለሀገር አይበጅም እና ሌላ ውድቀት እንዳይመጣ፡፡

በሌላ በኩል ለጥናት እና ምርምር የተፈጠረውን ሰው ቢሮክራሲ ውስጥ ከቶ አይዞህ ማለት ሀገሪቱን በአዳዲስ ግኝቶች እንዳያራቁታት ሰጋሁ፡፡ እንግዲህ እንዲህ ከቀጠለ ዞን እና ከተሞችም ቢሆን አንድ ዶክተር አናጣም ብለው ምን የመሰለውን ሀኪም የጤና መምሪያ ሃላፊ እናድርግህ እያሉ ሆስፒታሎቻችን አበሳ ውስጥ እንዳይገቡ ፋሽኗን ደጋግመን ብናጤናት ደስ ይለኛል፡፡ አለዚያ መጪውን ጊዜ ሌላ ስራ ያደክመናል፡፡ ያለ አግባብ የመጡ ዶክተሮችን ወደ ቦታቸው ለመመለስ እና ከፖለቲካው ለመነጠል ደግሞ ስንታገል እንከርማለን፡፡ DIRETUBENEWS

NO COMMENTS