የመንግሥት ሠራተኞች ፍልሰት ሃይ ባይ ይሻል

0
2548
የመንግሥት ሠራተኞች ፍልሰት
የሰው ሀብት አስተዳደር ምሁራን በአንድ ተቋምም ይሁን በአገር አቀፍ ደረጃ የሠራተኞች የፍልሰት መጠን ከ20 በመቶ በላይ ከሆነ ተቋሙ ወይንም አገሪቷ አደጋ ውስጥ ናቸው ብሎ መደምደም ይቻላል ይላሉ።

የሰው ሀብት አስተዳደር ምሁራን በአንድ ተቋምም ይሁን በአገር አቀፍ ደረጃ የሠራተኞች የፍልሰት መጠን ከ20 በመቶ በላይ ከሆነ ተቋሙ ወይንም አገሪቷ አደጋ ውስጥ ናቸው ብሎ መደምደም ይቻላል ይላሉ።

የቀድሞ ሲቪል ሰርቪስ ሚኒስቴር የአሁኑ የፐብሊክ ሰርቪስና የሰው ሀብት ሚኒስቴር አገር አቀፍ የመንግሥት ሠራተኞችን አስመልከቶ በ2007 ያወጣው መረጃ እንደሚያሳየው፤ በ87 የፌዴራል የመንግሥት መስሪያ ቤቶች ውስጥ ብቻ 66 ነጥብ ስምንት በመቶ የሚሆኑ ሠራተኞች በግል ምክንያት ሥራቸውን ለቀዋል። ይህም በባለሙያዎቹ ድምዳሜ መሠረት ከፍተኛ አደጋ የሚባል ነው።

የዓለም ባንክ በ1999 ዓ.ም «የኢትዮጵያ ሲቪል ሰርቪስ የቅጥርና የክፍያ ሁኔታ» በሚል ያካሄደው የጥናት ውጤት እንደሚያሳየው ደግሞ፤ ለመንግሥት ሠራተኞች ፍልሰት ምክንያቱ በመንግሥት፣ በግልና በበጎ አድራጎት ድርጅቶች መካከል ያለው የደመወዝና ጥቅማ ጥቅም ልዩነት ከፍተኛ መሆን፣ የመልካም አስተዳደር እጦት፣ የፖለቲካ ጣልቃ ገብነት፣ የትምህርትና ስልጠና ዕድል ፍትሐዊ አለመሆን የሚሉት ዋነኞቹ ናቸው።: ethpress

READ  የመንግስት አመራሮችን ጨምሮ በሙስና ወንጀል የተጠረጠሩ 130 ግለሰቦች በቁጥጥር ስር ዋሉ

NO COMMENTS