በአይነቱ የመጀመሪያ የሆነው የብረታ ብረት ማምረቻ ስራ ጀመረ

0
1089
ከጠፍጣፋ ብረት የተለያዩ ምርቶችን የሚያመርተው የዛን ዛን የብረታ ብረት ማምረቻ ፋብሪካ ስራ ጀመረ። የፋብሪካውን ስራ መጀመር ያበሰረው የኢትዮጵያ ኢንቨስትመንት ኮሚሽን ነው። በኢስተርን ኢንዱስትሪ ዞን በሶስት ምዕራፍ የሚሰራው ፋብሪካው በ23 ሚሊዮን ዶላር ካፒታል በ103 ሺህ ካሬ ሜትር መሬት ላይ ነው ያረፈው።

ከጠፍጣፋ ብረት የተለያዩ ምርቶችን የሚያመርተው የዛን ዛን የብረታ ብረት ማምረቻ ፋብሪካ ስራ ጀመረ። የፋብሪካውን ስራ መጀመር ያበሰረው የኢትዮጵያ ኢንቨስትመንት ኮሚሽን ነው።

በኢስተርን ኢንዱስትሪ ዞን በሶስት ምዕራፍ የሚሰራው ፋብሪካው በ23 ሚሊዮን ዶላር ካፒታል በ103 ሺህ ካሬ ሜትር መሬት ላይ ነው ያረፈው።

ኮሚሽነር ፍፁም አረጋ ዛን ዛን የብረታ ብረት ማምረቻ በአገሪቷ የብረታ ብረት ኢንዱስትሪ ጠፍጣፍ ብረት በመጠቀም የሚያመርት የመጀመሪያው ፋብሪካ መሆኑን ተናግረዋል።

በአገሪቷ ከወዳደቁ የብረት ቁርጥራጮች የሚመረቱ የብረታ ብረት ውጤቶች ብቻ እንደነበሩ የገለጹት ኮሚሽነሩ ዛን ዛን ግዙፍ የማምረቻ ጥሬ እቃዎችን ከውጭ በማስገባት እየሰራ መሆኑን ገልጸዋል።

ኮሪያ የብረታ ብረት ፋብሪካዎችን ተጠቅማ ትልልቅ መርከቦችና የብረት ውጤቶችን በማምረት ኢኮኖሚዋን ማሳደግ እንደቻለች የጠቆሙት ኮሚሽነሩ “ለአገራችን ዕድገት የብረታ ብረት ኢንዱስትሪው ጉልህ ድርሻ አለው” ብለዋል።

በኢንዱስትሪ ዞኑ ስራውን በይፋ የጀመረው የብረታ ብረት ማምረቻ ፋብሪካ ከጠፍጣፋ ብረቶች የስታፋ፣ አርማታና ሌሎች ለግንባታ ስራ የሚያገለግሉ ብረታ ብረቶችን በአጭር ጊዜ ማምረት እንደሚችል ጠቁመዋል።

“በተለያዩ አካባቢዎች የተገነቡና በመገንባት ላይ ያሉ ፋብሪካዎች በፍጥነት ወደ ስራ መግባት አገሪቷ የምትከተለውን የኢንዱስትሪ ፖሊሲ ትክክለኛነት ያሳያል” ብለዋል ኮሚሽነሩ።

አገሪቷ ለብረታ ብረት ምርቶች የምታወጣውን የውጭ ምንዛሬ ከማስቀረት በተጨማሪ በቀጣይ ጥሬ እቃዎችን በአገር ውስጥ ለማምረት የቴክኖሎጂ ሽግግር ይፈጥራል።

የፋብሪካው ዋና ስራ አስኪያጅ ጂያንግ ይ ዡ ፋብሪካው በዓመት እስከ 200 ሺህ ቶን ብረት ማምረት እንደሚችል ገልጸዋል።
የአገሪቷን የውጭ ምንዛሪ ወጪ ከመቀነሱ ባሻገር ለኢትዮጵያ መንግስት በዓመት እስከ 60 ሚሊዮን ብር የገቢ ግብር ያስገኛል ነው ያሉት።
“በብረታ ብረት ኢንዱስትሪ ዘርፍ በመሰማራት ለዜጎች የስራ ዕድል በመፍጠር ለአገሪቷ ዕድገት የበኩላችንን አስተዋፅኦ እናበረክታለን” ብለዋል።

READ  ከቀረጥ ነፃ መብትን ተጠቅመው ለሌላ አላማ ያዋሉ ባለሃብቶች ላይ እርምጃ እንደሚወሰድ ተገለጸ

በሁለቱ አገራት መካከል ያለውን የንግድና ኢንቨስትመንት ትስስር እንደሚያጎለብተው ገልጸው “በአሁኑ ወቅትም ለ60 ኢትዮጵያውያንና 25 ቻይናውያን የስራ ዕድል ተፈጥሮላቸዋል” ሲሉ ተናግረዋል። ena

NO COMMENTS