ስዊድን ለሀይል ማመንጫነት ከሌሎች ሀገራት ቆሻሻ ማስገባት ጀምራለች

0
1064
ለታዳሽ ሀይል ማመንጫ
የአለማችን ተመራጭ የሶላር ሀይል አቅራቢ እንደሆነች የሚነገርላት ስዊድን ከሌሎች ሀገራት ቆሻሻ መቀበል ጀምራለች። የስካንዲናቪያዋ ሀገር የሌሎች ሀገራትን ቆሻሻ ማስገባት የጀመረችው ለታዳሽ ሀይል ማመንጫ የምትጠቀመው የሀገር ውስጥ ቆሻሻ እጥረት በማጋጠሙ ነው ተብሏል።

የአለማችን ተመራጭ የሶላር ሀይል አቅራቢ እንደሆነች የሚነገርላት ስዊድን ከሌሎች ሀገራት ቆሻሻ መቀበል ጀምራለች።
የስካንዲናቪያዋ ሀገር የሌሎች ሀገራትን ቆሻሻ ማስገባት የጀመረችው ለታዳሽ ሀይል ማመንጫ የምትጠቀመው የሀገር ውስጥ ቆሻሻ እጥረት በማጋጠሙ ነው ተብሏል።

ግማሽ የሚሆነውን የኤሌክትሪክ ፍጆታዋን ከታዳሽ ሀይሎች የምታገኘው ስዊድን፥ እንደ አውሮፓውያኑ አቆጠጣጠር በ1991 በድንጋይ ከሰል ላይ ከፍተኛ ግብር የጣለች የመጀመሪያዋ ሀገር ናት።

ቆሻሻን የሚፀየፉት ስዊድናውያን ተፈጥሮን እና አካባቢን ለመጠበቅ ምን ማድረግ እንዳለባቸው ጠንቅቀው ያውቃሉ ተብሏል።
እያንዳንዱ የሀገሪቱ ዜጋ ማንኛውንም ነገር ከቤት ውጭ እንዳይጥል ሰፊ የግንዛቤ ማስጨበጫ ስራ መሰራቱንም ነው የሀገሪቱ የቆሻሻ አስወጋጅ እና በድጋሚ ጥቅም ላይ አዋይ ማህበር የኮሙዩኒኬሽን ዳይሬክተር አና ካሪን ግሪፕዋል የተናገሩት።

በዚህም ሊጠናቀቅ የሳምንታት እድሜ በቀረው 2016 ከ1 በመቶ በታች የስዊድናውያን ዜጎች የነፍስ ወከፍ ቆሻሻ ብቻ በቆሻሻ መድፊያ ስፍራ መቀበሩ ተጠቁሟል።

በሀገሪቱ ቆሻሻን ወደ ሀገር ውስጥ የማስገባቱን እና የማቃጠሉን ስራ የግል ኩባንያዎች እያከናወኑ የሚገኙ ሲሆን፥ ብሄራዊ የቆሻሻን መልሶ ጥቅም ላይ የማዋል ፖሊሲ ተቀርፆ ተግባራዊ በመደረግ ላይ ነው።

የድንጋይ ከሰልን በቆሻሻ የተካችው ስዊድን ቆሻሻን ጥቅም ላይ ለማዋል በሚሰሩ ፋብሪካዎቿ በክረምት ወቅት ቤት ማሞቂያዎችን የሚያቀርቡ በርካታ ኩባንያዎች አሏት።

ይሁን እንጂ የሀገሪቱ ቆሻሻን ለቤት ማሞቂያ የማዋል ሂደት ጥያቄ እየተነሳበት ነው።
ሀገሪቱ በአሁኑ ወቅት ከብሪታንያ ቆሻሻ እያስገባች ቢሆንም ጊዜያዊ መሆኑ ተገልጿል።
የአውሮፓ ህብረት አባል ሀገራት የሚያጠራቅሙት ቆሻሻ መጠን ተገድቧል።
በመሆኑም ለሌሎች ሀገራት ቆሻሻዎቻቸውን እንዲወስዱላቸው ለአገልግሎት ክፍያ ከሚሰጡ በራሳቸው ቆሻሻን ጥቅም ላይ የሚያውሉ ፋብሪከዎችን መገንባት እና የቆሻሻ አወጋገድ ስርአታቸውን ማስተካከል ላይ እንዲያተኩሩ ስዊድን መክራለች።ምንጭ፦independent

READ  በጀልባ ላይ በደረሰ አደጋ ከ 100 በላይ ስደተኞች የደረሱበት ጠፋ ተባለ

NO COMMENTS