በእሥራኤል ትውልደ ኢትዮጵያውያን ደም እንዳይለግሱ ተጥሎባቸው የነበረ እገዳ ተነሳላቸው

0
1247
ቤተ እሥራኤሎች ደም እንዳይለግሱ
ትውልደ ኢትዮጵያ ቤተ እሥራኤሎች ደም እንዳይለግሱ ተጥሎ የቆየው ዕገዳ ብዙ ክርከር የፈጠረ ነው፡፡ ነገሩ ከዘር መድልኦ ጋር ተገናኝቶ ሲያወዛግብም ከርሟል፡፡ ስለ ጉዳዩ የተጋለጠው ከ20 ዓመት በፊት “ማ አሪቭ” የተባለ የሀገሪቱ ጋዜጣ ትውልደ ኢትዮጵያ ቤተ እሥራኤሎች የሚለግሱት ደም እነሱ ሳያውቁት እንደሚወገድ ከፃፈ በኋላ ነው፡፡

የእሥራኤል መንግሥት በበኩሉ የኤች.አይ.ቪ ኤድስ ስርጭት ከፍተኛ በሆነባቸው አካባቢዎች ለአንድ ዓመትና ከዚያ በላይ ለሆነ ጊዜ የኖሩ ዜጐች ደም እንዳይለግሱ የጣልኩት ዕገዳ ነው ብሏል፡፡

የኤች አይ ቪ ኤድስ ስርጭት ከፍተኛ የሆነባቸው አካባቢዎች ተብለው የተለዩት ከሰሃራ በስተደቡብ ያሉ የአፍሪካ እንዲሁም የደቡብ ምሥራቅ እስያና የካሪቢያን ሀገራት ናቸው፡፡ ትውልደ ኢትዮጰያ ቤተ እሥራኤሎችም ደም እንዳይለግሱ የተከለከለው በዚሁ ምክንያት ነው ብሎ ነበር፡፡

አሁን ይህ እገዳ መነሳቱን የእሥራኤል የጤና ጥበቃ ሚኒስቴር ይፋ አድርጓል፡፡ ውሣኔው በእሥራኤል መንግሥት ተቃዋሚዎች መወደሱን ስለ ጉዳዩ የፃፈው ታይምስ ኦፍ እሥራኤል አስፍሯል፡፡ የተቃዋሚው መሪ ይስሃቅ ሔርዞግ በተቋም ደረጃ ትውልደ ኢትዮጵያ ቤተ እሥራኤሎች ላይ ሲፈፅም የቆየው መድልኦ መቅረቱ አስደስቶናል እንዳሉ ጋዜጣው ፅፏል፡፡

ከሠላሣ ዓመት ለሚበልጥ ጊዜ በትውልደ ኢትዮጵያ ቤተ እሥራኤሎች ላይ ተጥሎ የቆየ ዕገዳ እንደሆነ ሔርዞግ ማስታወሳቸውንም ጠቅሷል፡፡ በእሥራኤል ከአንድ ዓመት በታች ለሆነ ጊዜ የኖሩ ትውልደ ኢትዮጵያ ቤተ እሥራኤሎች ግን አሁንም ደም መለገስ አይችሉም ተብሏል፡፡ ትውልደ ብሪታንያ ቤተ እሥራኤሎችም በጎርጎሮሣውያኑ አቆጣር ከ1980 እስከ 1996 ባሉ ዓመታት ደም እንዳይለግሱ ተመሳሳይ ዕገዳ ተጥሎባቸው እንደነበር ጋዜጣው አስታውሷል፡፡ timesofisrael

READ  Beckham Works towards Ending HIV/AIDS Pandemic in Ethiopia

NO COMMENTS