አቶ ተሾመ አለማየሁ የልማት ባንክ ተጠባባቂ ፕሬዝዳንት ሆነው ተመደቡ

0
1258
አቶ ተሾመ አለማየሁ
Image: Ato Teshome Alemayehu

አቶ ተሾመ አለማየሁ የልማት ባንክ ተጠባባቂ ፕሬዝዳንት ሆነው ተመደቡ

አቶ ተሾመ አለማየሁ በድንገት ከፕሬዝዳንትነት ሥልጣናቸው የተሰናበቱትን አቶ ኢሳያስ ባሕረን ተክተው የኢትዮጵያ ልማት ባንክን በተጠባባቂ ፕሬዝዳንትነት እንዲመሩት ተመደቡ፡፡

አቶ ተሾመ በዚሁ ባንክ የሊዝ ፋይናንስ ም/ፕሬዝዳንት (Vice President – Lease Finance) ሆነው ሲያገለግሉ የቆዩና በልማት ባንክም ሆነ በብሔራዊ ባንክ በተለያዩ የኃላፊነትና የሙያ አገልግሎት ቦታዎች ላይ በመሥራት ከ30 ዓመታት በላይ የባንክ ሙያ ልምድን ያካበቱ ሰው ናቸው፡፡

በተለይ ሙስናንና ብልሹ አሠራርን በመጋፈጥ እንደሚታወቁም በቅርበት አብረዋቸው የሠሩ ባልደረቦቻቸው ምስክርነት ይሰጣሉ፡፡ ካላቸው የረጅም ጊዜ የባንክ ሥራ ልምድም ሆነ ከሥነ ምግባራቸው በመነሳትም ቀጣዩ የልማት ባንክ ፕሬዝዳንት ሊሆኑ እንደሚችሉ ይገመታል፡፡

DireTube News

READ  አራት ወጣቶችን አባብሎ ወደ ሳዑዲ በመላክ የአካል ጉዳት እንዲደርስባቸው ያደረገው ግለሰብ በእስራትና በገንዘብ ተቀጣ

NO COMMENTS