ኢትዮጵያዊው ምሁር የኢንጅነሪንግ ዘርፍ ተሻላሚ ሆኑ

0
1815
ኢትዮጵያዊው ምሁር
Image: ኤርባስ ግሩፕና ግሎባል ኢንጅነሪንግ ዲን ካውንስል

ኤርባስ ግሩፕና ግሎባል ኢንጅነሪንግ ዲን ካውንስል በጋራ በመሆን የ2016 የኢንጅነሪንግ ምሁር ማዕረግን በአሜሪካ ሞርጋን ዩኒቨርስቲ መምህር ለሆኑት ኢትዮጵያዊ ዶክተር ያዕቆብ አስታጥቄ መስጠቱን ያሆ ኒውስ እና የዩንቨርስቲው ድረ-ገጽ ገልጿል፡፡

ምህሩ ሽልማቱን የወሰዱት ከ17 አገራት ለውድድር ከተመረጡ 40 ምሁራን ብልጫ ወስድው ነው፡፡

ሽልማቱ በደቡብ ኮሪያ ሴኦል ከተማ መስጠቱን ደረ-ገጹ አስፍሯል፡፡

ዶክተር ያዕቆብ በአፍሪካ የዘርፉን ትምህርት ለማሳደግ እያደረጉት ያለው አስትዋፅኦም አበረታች መሆኑን ዘገባው ያረዳል፡፡

በአዲስ አበባ፣ በሀዋሳ፣ በባህር ዳር፣ ጅማ እና በደብረ ብርሃን ዩንቨርስቲዎች አገልግሎት እንደሚሰጡም የሞርጋን ዩንቨርስቲ ድረ-ገጽ ዘገባ ያስረዳል፡፣፡

ዶክትር ያዕቆብ አስታጥቄ በኢንጅንሪንግ ዘርፍ በሰጧቸው ግልጋሎቶች ሽልማት ሲያገኙ ይህ ለ6ኛ ጊዜ መሆኑ ሰፍሯል፡፡

እ.አ.አ በ2013 በአሜሪካ ከ27ሺህ በላይ የኢንጂነሪንግ ምሁራን ጋር ተወዳድርው የአሜሪካ ብሄራዊ ባለምጡቅ አምዕሮ የተባለውን ሽልማት ማግኘታቸውን ለትውስታ ዘገባው አስፍሯል፡፡

የሽልማቱ አላማ በመላው አለም ያሉ የኢንጅነሪንግ ባለሙያዎችን በማበረታታት ለፈጠራ እንዲነሳሱ ማድረግ እንደሆነ ተብራርቷል፡፡ ህዳር 8፣ 2009 EBC

READ  አረና ትግራይ ፓርቲ ስብሰባዬ በመንግስት ታገደብኝ ሲል ቅሬታ አቀረበ

NO COMMENTS