ሂላሪ ክሊንተን ከዶናልድ ትራምፕ በተሻለ ከፍተኛ ድምፅ እንዳገኙ ያውቃሉ

0
10338
ዶናልድ ትራምፕ አሸናፊ
Image: Senator Hilary Clinton

በአሜሪካ ምርጫ ዶናልድ ትራምፕ አሸናፊ ይሁኑ እንጂ ከፍተኛ ድምጽ ያገኙት ሂላሪ ክሊንተን ነበሩ ሲል ሜትሮ ኒውስ በዘገባው አስታውቋል ሆኖም ግን የአሜሪካ የምርጫ ህግ ለአሸናት ሊያበቃት አልቻለም ነው የተባለው፡፡

ዘጠኝ ሰአት አካባቢ ክሊንተን 59,299,381 ድምጽ ነበር ያገኙት ትራምፕ ደግሞ 59,135,740 ድምጽ ይህ ደግሞ ከዲሞክራት እጩዋ ያነሰ ድምጽ ነው፡፡

በአሜሪካ እጩዎች አሽናፊ ለመሆን ከህዝባዊ ድምጽ ይልቅ ልዩ ኤሌክትራል ድምፅ ትልቅ
ዋጋ አለው፡፡ በአንድ እስቴት ላይ አብዛኛውን ድምፅ እጩዎች ካገኙ ሁሉንም ልዩ ኤሌክትራል ድምፅ የሚሰጥባቸውን ማሸነፍ ይችላሉ፡፡

ከታች ከምስሉ እንደምትመለከቱት ሂላሪ ባጠቃላይ 60,467,601 ሲያገኙ ትራምፕ ደግሞ 60,072,551 አግኝተዋል።

Trump
Electoral Vote

በእንዲህ አይነቱ አሰራር እንግዲ እንደ ትራምፕ ያሉ መሪዋች ተጠቃሚ ሆነዋል፡፡ እንዲህ አይነቱ ሁኔታ የመከሰቱ ነገር ጠባብ ቢሆንም እንደ ሂላሪ እድል የገጠማቸው ግን ብዙ ናቸው ሲል የሜትሮ ዘገባ ያስረዳል፡፡

አልጎር ፣ ክሌቨርላንድ ፣ ታይደር እንዲሁም ጃክሰን በእንዲ አይነቱ አካሄድ ተጠቃሚ ናቸው፡፡ በ1960 ይህ የአሜሪካ ምርጫ አሰራር ትልቅ የክርክር አጃንዳ አስነስቶ እንደነበር ይታወሳል፡፡ እስካሁን ድረስ ይህን አሰራር ለመለወጥም ሆነ ለማሻሻል የተካሄደ እርምጃ አለመኖሩ የሜትሮ ዘገባ ያሳያል፡፡

DireTube News

READ  ዶናልድ ትራምፕ የተተቹባቸው አዳዲሶቹ ሹማምንት

NO COMMENTS