በ4 ሰዓታት ውስጥ የሚገጣጠመውና ያለ አሽከርካሪ የሚሄደው የጭነት ተሽከርካሪ

0
6989
ያለ ሹፌር
Image: Charge

ያለ ሹፌር በራሱ የሚሄደው የእቃ ማመላለሻ ተሽከርካሪ በፈረንጆቹ 2017 በጉዳናዎች ላይ መንቀሳቀስ ይጀምራል ተብሏል።

ተሽከርካሪው ቀለል ባሉ ቁሶች የተሰራ ሲሆን፥ በቀላሉ አንድ ሰው በ4 ሰዓታት ውስጥ ሊገጣጠመው እንደሚችልም ተገልጿል።

በእንግሊዝ የተሰራው ተሽከርካሪው ያለ አሽከርካሪ እንደሚሄድ የተገለፀ ሲሆን፥ በአሁኑ ጊዜም ከመንግስት ፈቃድ ለማግኘት ዝግጅት ላይ መሆኑም ተነግሯል።

የሀገሪቱ መንግስትም ያለ አሽከርካሪ የሚሄዱ መኪኖችን እንደ አውሮፓውያኑ አቆጣጣር በ2020 በጉዳናዎቹ ላይ ማየት ፍላጎት አለው ተብሏል።

ተሽከርካሪውን ያመረተው ኩባንያ ዳይሬክተር ሴቬርድሎቭ፥ “አሁን ላይ ያሉ ተሽከርካሪዎች ተቀባይነት የላቸውም፤ የድምጽ እና የአየር ብክለትን የሚያስከትሉ እንዲሁም ከአካባቢ ጋር በቀላሉ የሚዋሃዱ አይደሉም” ብለዋል።

“አሁን የተሰራው ተሽከርካሪ ግን ከድምፅ እና ከየር ብክለት የፀዳ እና ምቹ ነው” ሲሉ ተናግረዋል።

ኩባንያው የሰራቸው አዳዲሶቹ አሽከርካሪ አልባ ተሽከርካሪዎቹ ከ3 ነጥብ 5 እስከ 26 ቶን የመጫን አቅም እንዳላቸውም የኩባንያው ዳይሬክተር አስታውቋል።

ተሽከርካሪው ክብደትን ለመቀነስ በሚረዳ ቴክኖሎጂ ነው የሚሰራው የተባለ ሲሆን፥ ይህም የተሽከርካሪውን ክብደት ለመቀነስ ታስቦ መሆኑ ተገልጿል።

ተሽከርካሪው ያለ አሽከርካሪ መንቀሳቀስ የሚያስችለው ሶፍት ዌር ተሰርቶ ማለቁ የተነገረ ሲሆን፥ ከሀገሪቱ መንግስት ፈቃድ እንዳገኘ ተጭኖበት ወደ ስራ ይገባል ተብሏል።

ኩባንያው ተሽከርካሪዎቹን በቀጣዩ የፈረንጆቹ ዓመት በስፋት ለማምረት እቅድ የያዘ ሲሆን፥ በመጀመሪያው ዓመትም 10 ሺህ ተሽከርካሪዎችን ለመገጣጠም አቅድ ይዟል።

A self-drive electric delivery van, that could be on UK streets next year, has been unveiled at the Wired 2016 conference in London.

The vehicle’s stripped-back design and lightweight materials mean it can be assembled by one person in four hours, the firm behind it claims.
The vehicles will be “autonomous-ready”, for when self-drive legislation is in place, the firm said.

READ  CBE Launches Technology to Protect Customers from Fraud

The government wants to see self-drive cars on the roads by 2020.

“We find trucks today totally unacceptable. Loud, polluting and unfriendly,” said Denis Sverdlov, chief executive of Charge, the automotive technology firm behind the truck.
“We are making trucks the way they should be – affordable, elegant, quiet, clean and safe.”

He added: “We are removing all the barriers to entry for electric vehicles by pricing them in line with conventional trucks, giving every fleet manager, tradesperson or company, no matter how big or small, the opportunity to change the way they transport goods and make our towns and cities better places to live in.”

Charge plans to develop trucks in a range of sizes from 3.5 to 26 tonnes and is in talks with the major truck fleet firms.

DHL has previously said of the firm: “We see huge potential in the contribution they can make to advancing technology for commercial usages and the way we envisage the future of logistics.”

The vehicles will be built using ultra-lightweight composite materials that significantly reduce the weight of the vehicle, it said.

(ኤፍ.ቢ.ሲ) | ምንጭ፦ www.bbc.com

NO COMMENTS