ለጠቅላላ እውቀት ጠቃሚ መረጃዎች

0
6811
ለጠቅላላ-እውቀት
Image: Wikipedia

(Tesfisho Ras Teferi)

ፕላኔት ማለት ማንኛውም ከመሬት ከባቢ አየር ውጪ ያለ የተፈጥሮ አካል

1ኛ. በፀሃይ ዙሪያ የሚሽከረከር/የሚዞር

2ኛ. በዙሪያው ካሉ ሌሎች የተፈጥሮ አካላት የሚደርስበትን የግራቪቲ የሃይል ተፅእኖ ለመቋቋም የሚያስችለው የራሱን ተመጣጣኝ ግራቪቲ ለማመንጨት የሚያስችለው ግዙፍ አካል ያለውና የዚህ ግዙፍ አካሉ ቅርፅ ምሉእ ክብ የሆነ አካል፣

3ኛ. ይህ አካል በራሱ ምህዋር/Orbit ላይ በፀሃይ ዙሪያ በሚዞርበት/በሚሽከረከርበት ወቅት የራሱ ምህዋር ከሌላው ምህዋር ጋር የተለያየ (ምህዋሩ የሌላውን ምህዋር የማያቋርጥ/የማይነካ) ከሆነ ይህን አካል ፕላኔት ብለን መጥራት እንችላለን።

√ ድዋርፍ ፕላኔት/Dwarf planets/ ማለት የፕላኔት መጠን ያላቸው አካላት ሆነው ነገር ግን ፕላኔት ለመባል በፕላኔት ምደባ መስፈርት የፕላኔት ደረጃ/Status የሌላቸው አካላት (Dwarf planets) ይባላሉ። በዚህም መሰረት ድዋርፍ ፕላኔት ማለት ማንኛውም ከመሬት ከባቢ አየር ውጪ ያለ አካል ሆኖ…
1ኛ. በፀሃይ ዙሪያ የሚዞር/የሚሽከረከር አካል፣

2ኛ. ከሌላው በዙሪያው ካሉ አካላት ከሚደርስበት ስበት/የግራቪቲ ሃይል ተፅእኖን ለመቋቋም የሚያስችለውን የራሱን ተመጣጣኝ ስበት/ግራቪቲ ሃይል ማመንጨት የሚያስችለው ግዙፍ አካል ያለው፣

3ኛ. ነገር ግን በራሱ ምህዋር/Orbit ላይ በፀሃይ ዙሪያ ሲዞር/ሲሽከረከር በዙሪያው ካሉ ሌሎች አካላት ጋር የዚህ አካል ምህዋር ጥርት ያለ ልዩነት የሌለው (በምህዋሩ ላይ በፀሃይ ዙሪያ ሲዞር/ሲሽከረከር የራሱ ምህዋር የሌላውን ምህዋር የሚያቋርጥ ከሆነ) ይህ አይነት አካል ድዋርፍ ፕላኔት ወይም የፕላኔት መጠን ያለው ነገር ግን ፕላኔት ለመባል በፕላኔት ምደባ መስፈርት መሰረት የፕላኔት ደረጃ የሌላቸው አካላት (Dwarf planets) ይባላሉ።

√ እኛ የምንኖርባት ምድር/መሬት በምትገኝበት የሚልክዌይ ጋላክሲ ውስጥ 8 ፕላኔቶች እና 5 በግዝፈታቸው የፕላኔት መጠን ያላቸው ነገር ግን ፕላኔት ለመባል በፕላኔት ምደባ መስፈርት መሰረት የፕላኔት ደረጃ የሌላቸው አካላት (Dwarf planets) አሉ።

READ  መንትዮቹ ዮሐና እና ባና የመኪና አደጋ ደረሰባቸው

√ እነዚህ አካላት/ፕላኔቶች በፀሃይ ዙሪያ ሲዞሩ/ሲሽከረከሩ ሁለት አይነት እንቅስቃሴን ያደርጋሉ። አንደኛው በፀሃይ ዙሪያ የሚያደርጉት ሽክርክሪት ሲሆን ይህ እንቅስቃሴ ወቅቶችን/አመትን ለመለየት የሚረዳ እንቅስቃሴያቸው ነው። ሁለተኛው እንቅስቃሴያቸው በራሳቸው ዛቢያ/ምህዋር/Orbit ላይ የሚያደርጉት እንቅስቃሴ/ሽክርክሪት ሲሆን ይህ እንቅስቃሴያቸው ቀንና ሌሊት ለመለየት የሚረዳ እንቅስቃሴ ነው።

√ በነዚህ አካላት በተለይም የፕላኔት ደረጃ ባላቸው 8 ፕላኔቶች ላይ የቀንና የአመት ርዝመት በመሬት የጊዜ አቆጣጠር ሲለካ ምን ይመስላል? እንደሚከተለው አቀርበዋለሁ።

1ኛ. #ሜርኩሪ

√ ሜርኩሪ ፀሃይን አንድ ጊዜ ለመዞር/ለመሽከርከር (Earth days to orbit once around the sun) 88 የመሬት ቀናት ይፈጅባታል። ይህም ማለት ሜርኩሪ ላይ አንድ አመት ማለት 88 የመሬት ቀን ነው ማለት ነው።
ነገር ግን ሜርኩሪ በራሷ ምህዋር ላይ ስትሽከረከር (Earth days to rotate once on its own orbit) ዘገምተኛ ነች፣ ሜርኩሪ በራሷ ምህዋር ላይ ስትሽከረከር በሰከንድ 47.362km ፍጥነት አላት፣ በራሷ ምህዋር ላይ አንድ ጊዜ ለመዞር 175.96 የመሬት ቀን ይፈጅባታል። በዚህም ሜርኩሪ ላይ አንድ ቀን ማለት 175.96 የመሬት ቀን ነው ማለት ነው። #አይገርምም! ሜርኩሪ ላይ ቀኑ ከአመቱ ይበልጣል። ያ ማለት የሰው ልጅ ሜርኩሪ ላይ የሚኖር ቢሆን አንድ የማለዳ ፀሃይ ለማግኘት 175.96 የመሬት ቀን መጠበቅ ግድ ይለዋል።

2ኛ. #ቬኑስ

√ አንዴ በፀሃይ ዙሪያ ለመዞር – 224.7 የመሬት ቀን። ያ ማለት በቬኑስ ላይ አንድ አመት ማለት 224.7 የመሬት ቀን ነው።

√ ቬኑስ አንዴ በራሷ ዛቢያ/አክሲስ ላይ ለመሽከርከር 243 የመሬት ቀናት ይፈጅባታል። የሚገርመው ደግሞ ቬኑስ በራሷ አክሲስ ላይ የምትሽከረከረው ወደ ግራ/ከመሬት በተቃራኒ ነው።

READ  ሱዳን ከኢትዮጵያ 300 ሜጋ ዋት የኤሌክትሪክ ኃይል መግዛት እፈልጋለሁ አለች

3ኛ. #መሬት

እኛ የምንኖርባት ምድር/መሬት ከፀጋይ በ3ኛ ደረጃ ላይ የምትገኝ ሲሆን አንድ ጊዜ ፀሃይን ለመዞር 365 ¹∕⁴ ቀናት ወይም አንድ አመት ይፈጅባታል። በራሷ ምህዋር ላይ ለመዞር ደግሞ 24 ሰአት ወይም አንድ ቀን ይፈጅባታል።

4ኛ. #ማርስ

ማርስ ከፀሃይ በ4ኛ ደረጃ ያለች ፕላኔት ስትሆን ፀሃይን አንድ ጊዜ ለመዞር 687 ቀናትና 18.2 ሰአት ይኸውም በማርስ ላይ አንድ አመት ማለት በመሬት የጊዜ አቆጣጠር 1 አመት 320 ቀናትና 18.2 ሰአት ማለት ነው። ሌላው ማርስ በራሷ ዛቢያ ላይ አንዴ ለመሽከርከር 24 ሰአት ከ39 ደቂቃ የሚፈጅባት ሲሆን ይኸውም በማርስ ላይ አንድ ቀን ከመሬት ጋር እጅግ ተቀራራቢ መሆኑን ያሳያል፣ የ39 ደቂቃ ልዩነት ብቻ ነው ያለው። አንድ ቀን በማርስ ላይ ከመሬት አንድ ቀን በ39 ደቂቃ ይረዝማል።

☞ ከዚህ በኋላ የምንዘረዝራቸው ፕላኔቶች ማለትም ጁፒተር፣ ሳተርን እና ኔፕቲዩን (ፕሉቶ በግግር በረዶ የተሸፈነች ፕላኔት ስትሆን በ2006 አለማቀፉ የአስትሮኖመሮች ህብረት ፕሉቶን ከፕላኔትነት ወደ ድዋርፍ ፕላኔት ደረጃዋን ዝቅ አድርጎታል) በውጫዊው የፀሃይ ስርዓት ውስጥ የሚገኙ ፕላኔቶች ተብለው/Outer Solar System/ የሚጠሩ/የሚመደቡ ሲሆን አብዛኛዎቹ ወይም ሙሉ ለሙሉ በሚባል ደረጃ እነዚህ ፕላኔቶች በጋዝ የተሞሉ/ጋዛማ ፕላኔቶች ናቸው።

5ኛ. #ጁፒተር

ጁፒተር በግዝፈቱ የፕላኔቶች ንጉስ እየተባለ ይጠራል። ጁፒተር በግዝፈቱ መሬትን በ11 እጥፍ ይበልጣታል። ጁፒተር ፀሃይን አንዴ ለመዞር በመሬት የጊዜ አቆጣጠር 11.8618 አመት ወይም 4332.59 ቀናትን የሚፈጅበት ሲሆን ይህም ማለት በጁፒተር ላይ አንድ አመት መሬት ላይ 11.8618 አመት ወይም 4332.59 ቀናት ነው። ሌላው ጁፒተር በራሱ አክሲስ ላይ አንዴ ለመሽከርከር የሚፈጅበት 9 ሰአት ከ55 ደቂቃ ብቻ ነው። ይህም ማለት ጁፒተር ላይ አንድ ቀን ማለት 9 ሰአት ከ55 ደቂቃ ብቻ ነው ማለት ነው። በሌላ አገላለፅ ጁፒተር ላይ አንድ አመት ማለት 10,475.8 የጁፒተር ቀናት ነው።

READ  ጠቅላይ ሚኒስትር ኃይለማርያም የካቢኒያቸውን እጩ አባላት ለምክር ቤቱ እያቀረቡ ነው

6ኛ. #ሳተርን

ሳተርን በፀሃይ ዙሪያ አንዴ ለመዞር 10,759 የመሬት ቀናት ወይም 29 ½ የመሬት አመት ይፈጅባታል። በራሷ አክሲስ ላይ አንዴ ለመዞር ደግሞ 10 ሰአት ከ33 ደቂቃ ይፈጅባታል። ይህም ማለት በሳተርን ላይ አንድ ቀን 10 ከ33 ደቂቃ፣ አንድ አመት ደግሞ 29 ½ አመት ወይም 10,759 ቀናት ነው።

7ኛ. #ዩራኑስ

ዩራኑስ በፀሃይ ዙሪያ አንድ ጊዜ ለመዞር 84 አመት ወይም 30,688.5 ቀናት የሚፈጅባት ሲሆን በራሷ አክሲስ ላይ አንዴ ለመሽከርከር ደግሞ 17 ሰአት ከ14 ደቂቃ ይፈጅባታል። ይህም ማለት በዩራኑስ ላይ አንድ አመት ማለት በመሬት ላይ 84 ማለት ሲሆን አንድ ቀን ማለት ደግሞ 17 ሰአት ከ14 ደቂቃ ነው። ወይም በራሱ በዩራኑስ የጊዜ አቆጣጠር በዩራኑስ ላይ አንድ አመት ማለት 42,718 የዩራኑስ ቀናት ማለት ነው።

8ኛ. #ኔፕቲዩን

ኔፕቲዩን በፀሃይ ዙሪያ አንዴ ለመዞር 164.8 አመት ወይም 60,182 ቀናት የሚፈጅባት ሲሆን በራሷ አክሲስ ላይ አንዴ ለመሽከርከር ደግሞ 16 ሰአት ከ6 ደቂቃ ይፈጅባታል። ይህም ማለትበኔፕቲዩን ላይ አንድ አመት መሬት ላይ 164.8 አመት ወይም 60,182 ቀናት ማለት ሲሆን ኔፕቲዩን ላይ አንድ ቀን ማለት ደግሞ 16 ሰአት ከ6 ደቂቃ ማለት ነው።

DireTube.com

NO COMMENTS