የሥራ ባለደረባውን ለመግደል የሞከረው የፖሊስ አባል ቅጣት ተጣለበት

0
5526
የሥራ ባለደረባውን
Image: News.et

(እሸቴ አሰፋ)

ምክትል ሳጅን አሰፋ ጅራኔ ጥቅምት 18 ቀን 2007 ከምሽቱ 4 ሰዓት ግድም ረዳት ሳጅን መንግሥቱ አብዲን ከተረኛ ፖሊስ ጠመንጃ ነጥቆ ለመግደል በመሞከሩ ክስ ተመስርቶበታል፡፡

ካራቆሬ ፖሊስ ጣቢያ ቅጥር ግቢ ውስጥ በተፈጠረ የሥራ ግጭት ተከሳሽ ምክትል ሳጅን አሰፋ ጅራኔ የተረኛ ፖሊሱን አባል ክላሺንኮቭ ጠመንጃ ቀምቶና አቀባብሎ ረዳት ሳጅን መንግሥቱን ለመግደል ሲፈልግ እንደነበር የክስ መዝገቡ ያስረዳል፡፡

ከዚህም ሌላ ተከሳሹ የግል ተበዳዩን በቦክስ መትቶ ህመም እንዲሰማው ማድረጉም ተጨማሪ ክስ ሆኖ ቀርቦበታል፡፡

በአቃቤ ህግ የክስ መዝገብ ላይ መረዳት እንደሚቻለው ግድያው እንዳይፈፀም ያደረገው ሌላ የፖሊስ አባል ጠመንጃውን ስለቀማው ነው፡፡

ተከሳሹ በቦክስ መምታቱን አምኖ ነገር ግን የግድያ ሙከራ አለማድረጉን ለፖሊስ በሰጠው ቃል አስረድቷል፡፡
ጉዳዩን የሚያየው የፌዴራል ከፍተኛ ፍርድ ቤት ልደታ ምድብ 10ኛ ወንጀል ችሎት ተከሳሹ ፍርድ ቤት ቀርቦ ጉዳዩን እንዲከታተል ቀጠሮ ቢሰጥም ሊቀርብ ባለመቻሉ ጉዳዩን በሌለበት እንዲታይ ወስኗል፡፡

በዚሁ መሠረት ተከሳሽ ምክትል ሳጅን አሰፋ ጅራኔ በተከሰሳባቸው ሁለት ወንጀሎች ጥፋተኛ ነው ብሎ በ13 አመት ፅኑ እሥራት እንዲቀጣ ወስኖበታል፡፡

ፖሊስ ተከሳሹን አፈላልጐ እንዲይዝና ቅጣቱን እዲያስፈፅም መታዘዙን የፌዴራሉ ጠቅላይ አቃቤ ህግ የህዝብ ግንኙነት ኮሙኒኬሽን ጉዳዮች ባሰራጨው መግለጫ አመልክቷል፡፡

READ  የዘገየውና ያልተሟላው ፍትህ

NO COMMENTS