የአስቸኳይ ጊዜ አዋጁን ተፈጻሚነት የሚከታተል ኮማንድ ፖስት ተቋቁሟል

0
98212
ኮማንድ ፖስት
Image: Ethiopia

የአስቸኳይ ጊዜ አዋጁን አፈጻጸም የሚከታተልና በጠቅላይ ሚኒስትር ኃይለማርያም ደሳለኝ የሚመራ ኮማንድ ፖስት ተቋቁሟል።

ጠቅላይ ሚኒስትር ኃይለማርያም ለሕዝብ ባስተላለፉት መልዕክት እንደገለፁት፤ አዋጁ የኅብረተሰቡን ሠላምና ደህንነት በማስጠበቅ ዜጎች በሠላም ወጥተው መግባት የሚችሉበትን ሁኔታ ለመፍጠር ነው የታወጀው። ይህም ዜጎች የግል ሀብት በማፍራት ራሳቸውንና አገራቸውን በመጥቀም ያለ ስጋት እንዲኖሩ ያስችላል።

በመላው አገሪቱ ተፈጻሚ የሚሆነው ይህ አዋጅ በግልፅና በማያሻማ መንገድ የተዘጋጀ መሆኑንም አስረድተዋል። በሕዝብ ተወካዮች ምክር ቤት ገለልተኛ አካል በማቋቋም አፈጻጸሙን እየመረመረ ለሕዝቡ ይፋ የሚያደርግበት የአሰራር ስርዓት እንደተዘረጋለትም አክለዋል። አዋጁን የተመለከተ ዝርዝር ጉዳይ ለኅብረተሰቡ ይፋ የሚደረግ መሆኑንም አስታውቀዋል።

አዋጁ በሕገ መንገሰቱ አንቀጽ 93 መሰረት የታወጀ ነው።

በኢትዮጵያ ሕገ መንግስት አንቀጽ 93 መሰረት የአስቸኳይ ጊዜ አዋጅ የሚታወጀው አገሪቷ ለሚያጋጠማት ችግር ፈጣን መፍትሄ ለመስጠት እንዲቻል መሆኑን አንድ የሕግ ባለሙያ ተናገሩ።

የሚኒስትሮች ምክር ቤት የአገሪቷን ህልውና ለማስጠበቅና የሕዝብ ሠላም፣ ፀጥታና ደህንነት ላይ የተደቀነውን ከፍተኛ ስጋት ለመቀልበስ ከትናንት ጀምሮ የሚተገበር የአስቸኳይ ጊዜ አዋጅ ማወጁ ይታወቃል።

ይህን ተከትሎ ለኢዜአ አስተያየታቸውን የሰጡት የሲቪል ሰርቪስ ዩኒቨርሲቲ መምህር ረዳት ፕሮፌሰር ተስፋዬ አባተ እንደገለጹት፤ የሕገ መንግስቱ አንቀጽ 93 ንኡስ አንቀጽ ‘ሀ’ እንደሚያስቀምጠው ሕገ መንግስታዊ ስርዓቱን አደጋ ላይ ሊጥል የሚችል ነገር ሲከሰትና በመደበኛ ሕግ የማስከበር ስራ መቋቋም ሳይቻል ሲቀር የአስቸኳይ ጊዜ አዋጅ ይታወጃል።

አዋጁ አገሪቷ የተለየ ነገር ሲገጥማትና ለችግሩ አስቸኳይ መፍትሄ ለመስጠት ሲታሰብ የሚወጣ መሆኑን ነው የገለጹት። ረዳት ፕሮፌሰር ተስፋዬ እንደተናገሩት፤ የሕዝቡ ሠላምና ጸጥታ ስጋት ውስጥ በመውደቁና ሁኔታውን በመደበኛ ህግ የማስከበር ስርዓት መቀልበስ እንደማይቻል በመታመኑ የአስቸኳይ ጊዜ አዋጁ ታውጇል።

READ  Ethiopia's Christian Orthodox Church Celebrates Meskel

“አንቀጽ 93 ንዑስ አንቀጽ ‘ሀ’ እንደሚያስቀምጠው ሕገ መንግስታዊ ስርዓቱን አደጋ ላይ ሊጥል የሚችል ነገር ሲከሰትና በመደበኛ ሕግ ማስከበር ሥራ መቋቋም ሳይቻል ሲቀር ነው የሚታወጀው” ብለዋል።

ሕገ መንግስቱ በአስቸኳይ ጊዜ አዋጅ ፖለቲካዊና ዴሞክራሲያዊ መብቶች ሊገደቡ የሚችሉበት ሁኔታ ሊኖር እንደሚችልም አስቀምጧል ነው ያሉት።

“ያ ማለት ግን በምንም ምክንያት የማይገደቡ የመብት ጉዳዮች መኖራቸውም መዘንጋት የለበትም” ሲሉ አክለዋል።

ከእነዚህ መካከልም በሕገ መንግስቱ አንቀጽ አንድ የተቀመጠው የኢትዮጵያ ፌዴራላዊ ዴሞክራሲያዊ ሪፐብሊክ መንግስት መሆኑን መቀየር ወይም ደግሞ መገደብ እንደማይቻል ገልፀዋል።

በአስቸኳይ ጊዜ አዋጁ መሠረት በቁጥጥር ስር የሚውሉ ሰዎች ከሁሉም በላይ ሰብዓዊ መብታቸው እንዲጠበቅ በሕገ መንግስቱ አንቀጽ 18 መስፈሩን ጠቁመዋል።

“በአዋጁ መሠረታዊ ሰብዓዊ መብቶች አይጣሱም ሲባልም በአንቀጽ 18 መሠረት በምንም ምክንያት ኢ-ሰብዓዊ ድርጊቶች የተከለከሉ ናቸው ማለት ነው” ብለዋል።

በተጨማሪም አዋጁ በሚተገበርበት ወቅት በአንቀጽ 25 ላይ የተቀመጠው ሰዎች ሁሉ በሕግ ፊት እኩል መሆናቸው፣ በሰዎች መካከል ምንም ዓይነት ልዩነት ሳይደረግ እኩል ጥበቃ እንዲደረግላቸውና በዘር፣ በኃይማኖትና በሌሎች ነገሮች ልዩነት ሳይኖር የሕግ ዋስትና እንዲያገኙም ይደረጋል ነው ያሉት።

በሕገ መንግስቱ አንቀጽ 39 ንኡስ አንቀጽ አንድና ሁለት ላይ የሰፈረው የአገሪቷ ብሔር ብሔረሰቦችና ሕዝቦች የራሳቸውን ዕድል በራሳቸው የመወሰን መብታቸው ሊገደብ እንደማይችልም ተናግረዋል በአዋጁ።

“ስለዚህ አሁን በኢትዮጵያ እየተተገበረ ያለው የአስቸኳይ ጊዜ አዋጅ እነዚህ መሠረታዊ ሰብዓዊ መብቶች እንደማይጣሱበት ተስፋ አለኝ” ሲሉ አስተያየታቸውን ሰጥተዋል።

በመሆኑም ሕብረተሰቡ ይህን ታሳቢ በማድረግ ከማናቸውም ጊዜ በበለጠ የፀጥታ ስራውን በኃላፊነት ከሚያከናውኑ አካላት ጋር መተባበር ይጠበቅበታል ብለዋል።

READ  Ten Million Refugees Hosted in Ten Countries

ለዚህ አካል አግባብነት ያለውን መረጃ የመስጠት፣ ወደ ሕገ ወጥ እንቅስቃሴ አለመግባትና አዋጁን እንዲሁም የአገሪቷን ሕግ የማክበር ሁኔታዎች መኖር እንዳለባቸው አስረድተዋል።

በአስቸኳይ ጊዜ አዋጁ በሕገ-መንግስቱ የተደነገጉት መሰረታዊ የሰብዓዊ መብቶችና በቪየና ኮንቬንሽን ጥበቃ የሚደረግላቸው ዲፕሎማቲክ መብቶች መተግበር እንዳለባቸውም ገልጸዋል። ENA

NO COMMENTS