ምስራቅ አፍሪካ ሶስት ታላላቅ ሰዎችን አጣች

0
2588
በኢትዮጵያ እና በኤርትራ
Image: East Africa Lost this Mens

በዚህ ሳምንት በኢትዮጵያ እና በኤርትራ ታላላቅ ሰዎች ሞተዋል። 

ጄነራል ለገሠ ተፈራ አረፉ

የኅብረተሰብዓዊት ኢትዮጵያ ጀግና ሜዳይ ተሸላሚ የነበሩት ብሪጋዲየር ጄነራል ተፈራ ለገሠ ዛሬ አረፉ፡፡
የኅብረተሰብዓዊት ኢትዮጵያ ጀግና ሜዳይ ተሸላሚ የነበሩት ብሪጋዲየር ጄነራል ተፈራ ለገሠ ዛሬ አረፉ፡፡ብሪጋዲየር ጄነራል ለገሠ አሜሪካ ውስጥ በሕክምና ሲረዱ መቆየታቸውን ለቤተሰቡ ቅርበት ያላቸው ምንጮች ለቪኦኤ ገልፀዋል፡፡

ብ/ጄነራል ለገሠ ተፈራ ከሃረር የጦር አካዳሚ በ1959 ዓ.ም ተመርቀው የኢትዮጵያ አየር ኃይልን መቀላቀላቀላቸውንና የጄት አብራሪና መምህር ሆነው ማገልገላቸውን የሕይወታቸው ታሪክ ይናገራል፡፡

የዚያድ ባሬ ሶማሊያ ጦር በ1960ዎቹ መጨረሻ ኢትዮጵያን በምሥራቅና በደበቡብ ምሥራቅ በኩል ወርሮ በነበረ ጊዜ የዘጠነኛው ስኳድሮን ባልደረባ የነበሩት ተዋጊ ጄት አብራሪ ጄነራል ለገሠ ተፈራ አምስት የሶማሊያ ጦር አይሮፕላኖችን በአየር ላይ ውጊያ መትተው መጣላቸው ይነገርላቸዋል፡፡

ጄነራል ለገሠ ተፈራ በጦር እሥረኛነት ለአሥራ አንድ ዓመታት ሶማሊያ ውስጥ ከቆዩ በኋላ ወደ ሃገራቸው ሲገቡ ወደ ኢትዮጵያ አየር ኃይል ተመልሰው በበረራ አስተማሪነት አገልግለዋል፡፡

ግንባር ላይ ለፈፀሙት ጀብዱም የጦር ሜዳ ጀብዱ ሜዳይና የኅብረተሰብዓዊት ኢትዮጵያ ጀግና ሜዳይ በወቅቱ የኢትዮጵያ መሪ ኮሎኔል መንግሥቱ ኃይለማርያም ተጠልቆላቸዋል፡፡

ብሪጋዲየር ለገሠ ተፈራ ኮ/ል መንግሥቱ ኃይለማርያምን ከሥልጣን ለመገልበጥ የተሞከረው የ1983ቱ ኩዴታ ሲከሽፍ ወደ አሜሪካ ተሰድደው እስከ ሕልፈታቸው እዚያው ኖረዋል፡፡

ብሪጋዲየር ለገሠ ተፈራ ሦስት ልጆችን አፍርተዋል፡፡

አምባሳደር ግርማ አስመሮም

በተባበሩት መንግሥታት ድርጅት የኤርትራ ቋሚ ተጠሪ ሆነው ሲያገለግሉ የቆዩት አምባሳደር ግርማ አስመሮም አረፉ፡፡
ዋሺንግተን ዲሲ —
በተባበሩት መንግሥታት ድርጅት የኤርትራ ቋሚ ተጠሪ ሆነው ሲያገለግሉ የቆዩት አምባሳደር ግርማ አስመሮም አረፉ፡፡

READ  ከድንበሮች 50 ኪሎ ሜትር ገባ ብሎ ያሉ ስፍራዎች ቀይ ዞን ተባሉ

አምባሣደሩ ትናንት ኒው ዮርክ ላይ በስድሣ ስድስት ዓመት ዕድሜአቸው ማረፋቸው የታወቀው ዛሬ ሲሆን ላለፉት ዘጠኝ ወራት በሕመምና በሕክምና ላይ እንደነበሩ ታውቋል፡፡

አምባሣደር ግርማ ወደ ኒው ዮርክ ከመላካቸው በፊት በኢትዮጵያና በአፍሪካ ኅብረት፣ እንዲሁም በዩናይትድ ስቴትስና በካናዳ የኤርትራ አምባሣደር ሆነው አገልግለዋል፡፡

አምባሣደር ግርማ ዋሺንግተን ዲ.ሲ. ከሚገኘው አሜሪካን ዩኒቨርሲቲ በዓለምአቀፍ ግንኙነቶች በማስተርስ ዲግሪ ተመርቀዋል፡፡

አምባሣደር ግርማ አስመሮም በወጣትነት ዕድሜአቸው የኢትዮጵያ እግር ኳስ ብሄራዊ ቡድን ተጫዋችና በአምስት ቁጥር ቦታ ተከላካይ፤ እንዲሁም በሰባት ቁጥር ቦታ የሚሰለፉ አጥቂ ነበሩ፡፡

አምባሣደር ግርማ ባለትዳር ነበሩ፡፡

ኢንጂነር ኃይሉ ሻወል አረፉ

ከቅንጅት ለአንድነትና ለዴሞክራሲና ከመላ ኢትዮጵያ አንድነት ድርጅት – መኢአድ መሥራቾችና መሪዎች አንዱ የነበሩት አቶ ኃይሉ ሻወል አረፉ፡፡

ከቅንጅት ለአንድነትና ለዴሞክራሲና ከመላ ኢትዮጵያ አንድነት ድርጅት – መኢአድ መሥራቾችና መሪዎች አንዱ የነበሩት አቶ ኃይሉ ሻወል አረፉ፡፡

አቶ ኃይሉ ሻወል በሰማንያ ዓመት ዕድሜአቸው ዛሬ ያረፉት በሕክምና ሲረዱ በነበረባት ታይላንድ መሆኑን ለቪኦኤ ቅርበት ያላቸው ምንጮች ገልፀዋል፡፡

አቶ ኃይሉ ሻወልን ለሕልፈት ያበቃቸው የጤና ችግር ምን እንደሆነ ለጊዜው እያጣራን ቢሆንም እራሣቸው በፃፉት መፅሐፍ ላይ እሥር ቤት ሣሉ በገጠማቸው ቅዝቃዜ ምክንያት አከርካሪያቸው ላይ ሕመም ይሰማቸው እንደነበረ ጠቁመዋል፡፡

ላለፉት ሁለት ዓመታትም በብርቱ ሲታመሙ መቆየታቸው ተገልጿል፡፡

የአቶ ኃይሉ ሻወል (ኢንጂነር)አስከሬን ነገ፤ ዓርብ አዲስ አበባ ይገባል ተብሏል።

ተጨማሪ መረጃ ባገኘን ጊዜ ይህንን ዜና እናዳብራለን፡፡ በነገ የአየር ሥርጭታችን ላይ ሥፋት ያለው ዘገባ ለማቅረብ እንጥራለን፡፡

NO COMMENTS