የኢሬቻ በዓል ላይ በተነሳ ግርግር የበርካታ ሰዎች ህይወት ጠፍቷል

0
90537
የኢሬቻ በዓል ግርግር
Image: Irecha Protest

የኢሬቻ በዓል በቢሾፍቱ ሆራ አርሰዲ ሃይቅ የበዓሉ አክባሪዎች ከሌሊቱ ፲ ሰዓት ጀምሮ በስፍራው በመገኘት ስያከብሩ ቆይተው ወደ መገባደዱ ላይ በተነሳ ግርግር ከ70 በላይ የሚሆኑ ሰዎች ህይወት መጥፋቱን ከስፍራው የሚገኘው ባልደረባችን ነግሮናል።

በኦሮሞ ሕዝብ የአኗኗር ዘይቤ ውስጥ ትልቅ ስፍራ የሚሰጠው ይህ በዓል ላይ ከአራት ሚሊዮን በላይ ሰዎች ታድመውበታል። የዛሬው ኢሬቻ ከፍተኛ የሆነ ቁጥጥር የተደረገበትና ከ4 ሚሊዮን በላይ ሰዎችን ያስተናገደ በዓል ነበር። መንግስትን በመቃወምም እጃቸውን በማጣመር ተቃውሞ የገለፁ ሲኖሩ፣ ሄሊኮፕተሮች ሲበሩም መታየታቸውን ቀደም ብለን ዘግበን ነበር።

የመንግስት ኮሚኒኬሽን በዛሬው ግርግር ዙሪያ ይህንን መግለጫ አውጥቷል።

በኢሬቻ በዓል መስተጓጎልና የሰው ህይወት መጥፋት ላይ
ከመንግስት ኮሙኒኬሽን ጉዳዮች ጽ/ቤት የተሰጠ መግለጫ

የኢሬቻ በዓልን ባህላዊ አከባበር ጠብቆ ለማክበር የኦሮሞ ህዝብ አባገዳዎችና የኦሮሚያ ክልላዊ መንግስት ያደረጉት ሰፊ ቅድመ ዝግጅት በሁከት ፈጣሪ ኃይሎች ምክንያት ተስተጓጉሏል፡፡

በበዓሉ አከባበር ላይ አባገዳዎች በዓሉን በሰላም እየመሩ እያለ ለሁከት አስቀድመው የተዘጋጁ ኃይሎች ሁከትና ግርግር በማስነሳታቸው በዓሉ እንደተፈለገው ሳይጠናቀቅ ቀርቷል፡፡ ሁከት ፈጣሪዎቹ ባስነሱት ሁከት በተፈጠረ ግርግር በመረጋገጥ የሰው ህይወት ጠፍቷል፡፡

የኢፌዴሪ መንግስት የገዳ ስርዓትን በዩኔስኮ ለማስመዝገብና የኢሬቻ በዓል ባህላዊ ይዘቱን ጠብቆ እንዲከበር ከፍተኛ ጥረት እያደረገ እያለ የኦሮሞ ህዝብ የገዳ ስርዓት አካል የሆነው የኢሬቻ በዓል በዚህ መልክ በመስተጓጎሉና የሰው ህይወት በመጥፋቱ ከፍተኛ ሃዘን ተሰምቶታል፡፡

ሁከቱ በፈጠረው ግርግርና መረጋገጥ ህይወት መጥፋቱ የታወቀ ሲሆን በርካታ ተጎጂዎች ወደህክምና ቦታ ተወስደዋል፡፡ የኢፌዴሪ መንግስት ዝርዝር መረጃውን በቀጣይ የሚያሳውቅ ሆኖ ለዚህ ጥፋት ተጠያቂ የሆኑ አካላትንም ለህግ እንደሚያቀርብ ቃል ይገባል፡፡

READ  በሳምንት ውስጥ በኦሮሚያ ክልል ከ130 በላይ ኩባንያዎች ወደሙ

በስፍራው ያለውን ሁኔታ ከዚህ ቪዲዮ ይመልከቱ

ሁከቱ በፈጠረው ግርግርና መረጋገጥ ህይወት መጥፋቱ የታወቀ ሲሆን በርካታ ተጎጂዎች ወደህክምና ቦታ ተወስደዋል፡፡ የኢፌዴሪ መንግስት ዝርዝር መረጃውን በቀጣይ የሚያሳውቅ ሆኖ ለዚህ ጥፋት ተጠያቂ የሆኑ አካላትንም ለህግ እንደሚያቀርብ ቃል ይገባል፡፡

የዘንድሮው የኢሬቻ በዓል ትላንት በዋዜማው ዕለት በተለያዩ ዝግጅቶች የደመቀ ሲሆን ዛሬ ግን በቢሾፍቱ ሆራ አርሴዲ ሀይቅ በርካታ ሕዝብ ህይወቱን ያጣበት ሆኗል።

NO COMMENTS