ፍርድ ቤቱ ኮሎኔል ደመቀ ዘውዱ በማረፊያ ቤት በቀጠሮ እንዲቆዩ ለተጠየቀበት መዝገብ ብይን ሰጠ

0
85211
ደመቀ ዘውዱ
Image: ደመቀ ዘውዱ

ጎንደር መስከረም 18/2009 የሰሜን ጎንደር ዞን ከፍተኛ ፍርድ ቤት ከግድያ ወንጀል ጋር በተያያዘ በተጠረጠሩት ኮሎኔል ደመቀ ዘውዱ ላይ በፖሊስ አመልካችነት የተከፈተውንና በጊዜ ቀጠሮ በማረፊያ ቤት እንዲቆዩ ጥያቄ የቀረበበትን መዝገብ መርምሮ ብይን ሰጠ።

ፖሊስ በተጠርጣሪው ላይ የወንጀል ምርመራ በመጀመሩ የጊዜ ቀጠሮ እንዲሰጠው ሐምሌ 8/2008ዓ.ም በተጻፈ ደብዳቤ ቢጠይቅም ከተጠቀሰው ጊዜ ጀምሮ በጸጥታ ችግር ምክንያት ተጠርጣሪውን በአካል ፍርድ ቤት ለማቅረብ ሳይችል ቆይቷል፡፡

ከፍተኛ ፍርድ ቤቱ ፖሊስ ምርመራውን ሊያጣራ የሚያስችለውን ያክል ምክንያታዊ ጊዜ ስላገኘ ተጨማሪ ጊዜ ሊሰጥ እንደማይገባ አስታውቋል።

በተጨማሪም ፖሊስ መስከረም 3/2009 ዓ.ም በጻፈው ደብዳቤ ምርመራውን አጠናቅቆ ለዞኑ ፍትህ መምሪያ የምርመራ መዝገቡን በማስተላለፉ በወንጀለኛ መቅጫ ስነ ስርአት ህግ ቁጥር 59.1 እና 109.1 መሰረት ተጨማሪ የጊዜ ቀጠሮ መስጠቱ ተገቢ እንዳልሆነ ፍርድ ቤቱ ገልጿል።

የፖሊስ የምርመራ መዝገብ የደረሰው የሰሜን ጎንደር ዞን ፍትህ መምሪያም በወንጀለኛ መቅጫ ስነ ስርአት ህግ ቁጥር 109.1 መሰረት ክስ እንዲያቀርብ ከፍተኛ ፍርድ ቤቱ አዝዟል፡፡

የጊዜ ቀጠሮና የዋስትና ጥያቄዎች ተፈጥሮአዊ ባህርያቸው የተለያየ በመሆኑ በዚሁ መዝገብ በዋናነት የቀረበው የጊዜ ቀጠሮ ይፈቀድልኝ የሚል በመሆኑ ተጠርጣሪው በጠበቆቹ እየታገዘ በሌላ እራሱን በቻለ መዝገብ የዋስትና ጥያቄ የማቅረብ መብቱ የተጠበቀ መሆኑን ፍርድ ቤቱ አስታውቋል፡፡

የኮሎኔል ደመቀ ጠበቃ በበኩላቸው ከደንበኛቸው ጋር በመመካከር አስተያየት በጽሁፍ ለማቅረብ የ15 ቀን ጊዜ እንዲሰጣቸው ፍርድ ቤቱን ጠይቀዋል፡፡

Colonel Demeke Zewdu Speech

የፌደራል ፖሊስ ኮሚሽን በግድያና በሽብር ወንጀል በተጠርጣሪው ላይ ላቀረበው የምርምራ የጊዜ ቀጠሮ ጥያቄም ከፍተኛ ፍርድ ቤቱ የ15 ቀን የምርመራ ጊዜ ፈቅዷል፡፡

READ  ኢትዮጵያ በአውሮፓውያኑ 2020 የአለማችን 66ኛዋ ባለ ትልቅ ኢኮኖሚ ሀገር ትሆናለች

ፍርድ ቤቱ የግራ ቀኙንና የተጠሪውን አስተያየት ለመቀበል ለጥቅምት 3 ቀን 2009ዓ/ም ቀጠሮ ሰጥቷል፡፡

NO COMMENTS

LEAVE A REPLY