አትሌት አልማዝ አያና የኒሳን መኪና ሽልማት ትቀበላለች

0
17905
አልማዝ አያና
Almaz Ayana Car

በ31ኛው የሪዮ ኦሎምፒክ እና በ15ኛው የሪዮ ፓራሎምፒክ ውድድር ለተሳተፉት የኢትዮጵያ የልዑካን ቡድን አባላት የዕውቅናና የማበረታቻ ሽልማት ማበረታቻ በብሔራዊ ቤተ መንግስት እየተሰጠ ይገኛል።

ኢትዮጵያ በሪዮ ኦሎምፒክ በአትሌቲክስ፣ በውሃ ዋናና ብስክሌት ተሳትፎዋ አራት የወርቅ፣ አራት የብርና አራት የነሐስ በድምሩ 12 ሜዳሊያዎችን ለማምጣት አቅዳ አንድ ወርቅ፣ ሁለት ብርና አምስት ነሐስ በጠቅላላው ስምንት ሜዳሊያዎችን ይዛ መመለሷ ይታወቃል።

ይህም ውጤቷ ባለፉት ሁለት አስርት ዓመታት ውስጥ ከተካሄዱት ኦሊምፒኮች ያነሰ ሆኖ ተመዝግቧል።

በሪዮ ኦሎምፒክስ በተካሄደው የሴቶች የ10ሺህ ሜትር የሩጭ ውድድር ኢትዮጵያዊቷ አትሌት አልማዝ አያና ክብረ ወሰን በመስበር ለኢትዮጵያ ወርቅ ያመጣች ብቸኛ አትሌት ስትሆን በዛሬው ዝግጅት ኒሳን መኪና እንደምት ሸለም ታውቋል።

UPDATE: በውድድሩ የወርቅ ሜዳሊያ ላስገኘችው አልማዝ አያና 1 ነጥብ 5 ሚሊየን ብር የሚያወጣ መኪና ተሸልማለች።

በአጠቃላይ ለኦሎምፒክ ቡድኑ አባላት 6 ሚሊየን ብር ሽልማት ተከፋፍሏል።

READ  ለጠቅላላ እውቀት ጠቃሚ መረጃዎች

NO COMMENTS

LEAVE A REPLY